Loading
Singer
ያን ፡ ዓመት ፡ እያስታወስኩኝ ያንን ፡ ወር ፡ እያስታወስኩኝ ያንን ፡ ቀን ፡ እያስታወስኩኝ ከአውሬው ፡ አፍ ፡ በአንተ ፡ እንደዳንኩኝ አውቃለሁ ፡ ክብርን ፡ ምሥጋናን ፡ ለአንተ ፡ አመጣለሁ (፬x) ስንት ፡ መስከረም ፡ ስንት ፡ ጥቅምት ከእባብ ፡ ከጊንጡ ፡ የዳንኩበት ስንት ፡ ህዳር ፡ ነበር ፡ ስንት ፡ ታህሳስ ከሞት ፡ ያዳንከኝ ፡ ደርሰህ ፡ ኢየሱስ ስንት ፡ ጥር ፡ አልፏል ፡ ስንት ፡ የካቲት አለቀልኝ ፡ ብዬ ፡ ያልኩበት ስንት ፡ መጋቢት ፡ ስንት ፡ ሚያዚያ ሃዘን ፡ ሲሆነኝ ፡ መውጫና ፡ መግቢያ ግንቦትስ ፡ ሰኔ ፡ ሐምሌ ፡ ነሃሴ የጭንቅን ፡ ቀን ፡ አይቷል ፡ ይህ ፡ ነፍሴ በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ ደርሰህ ፡ ያዳንከኝ እንዳመሰግን ፡ ዛሬን ፡ ሰጠኸኝ (፪x) በጠዋት ፡ በቀትር ፡ ባመሻሽ ፡ በሌሊት ስራህን ፡ ለማሰብ ፡ ብራመድ ፡ የኋሊት ትዝ ፡ የሚሉኝ ፡ ማስታውሳቸው የአንተን ፡ ማዳን ፡ ያየሁባቸው እኮ ፡ እነዚያ ፡ የሄዱት ፡ አርቦች ሃሙስ ፡ ቅዳሜ ፡ ብዙ ፡ እሁዶች እሮቦቼ ፡ ማክሰኞ ፡ ሰኞ ያልፍኳቸው ፡ ማዳንህ ፡ ገኖ ይሁኑልኝ ፡ ለመታሰቢያ የአንተን ፡ ማዳን ፡ ሁሌ ፡ ለማውሪያ እንዲህ ፡ ልበል ፡ ክበር ፡ ተመስገን በአንተ ፡ ምህረት ፡ አለፈ ፡ ያ ፡ ቀን አውቃለሁ ፡ ክብርን ፡ ምሥጋናን ፡ ለአንተ ፡ አመጣለሁ (፬x) በሌሊት ፡ ከእንቅልፌ ፡ በድንገት ፡ ስነቃ ቀኑን ፡ ላለማየት ፡ እል ፡ ነበር ፡ ባልነጋ ባልነጋ ፡ ስላልኩኝ ፡ መች ፡ ቀርቶ ፡ ሳይነጋ ቀኑን ፡ እንዳዘንኩኝ ፡ እደርስ ፡ ነበር ፡ ምሸትጋ በጉስቁልናዬ ፡ አዘንክልኝና ለነፍሴ ፡ ሰጠሃት ፡ የመጽናናት ፡ መና ሌሊቶቼም ፡ ሆኑ ፡ መዝሙር ፡ መቀበያ ቀኖቼም ፡ የአንተን ፈቃድ ፡ ማገልገያ አውቃለሁ ፡ ክብርን ፡ ምሥጋናን ፡ ለአንተ ፡ አመጣለሁ (፬x)