Loading
Singer
ያምላኬ ፡ ጉዳይ ፡ ከበደብኝ ቅጥሩ ፡ ፈርሶ ፡ ስላየሁኝ ልቤን ፡ ላስታመው ፡ ደግሞ ፡ ምግብ ፡ አልበላ ቅጥሩ ፡ ታድሶ ፡ ካላየሁማ ኧኸ ፡ ጦቢያው ፡ ሰምበላት ኧኸ ፡ ውረድ ፡ ሲሉኝ ቅጥር ፡ ልሰራ ፡ ሄጃለሁኝ (፪x) ና ፡ ውረድ ፡ ሲሉኝ (፫x) ስፍራው ፡ ተመችቶኝ ፡ እዛው ፡ ቀረሁኝ አልወርድም ፡ አልወርድም ፡ ከተራራው ፡ ላይ የእግዚአብሔርን ፡ ክብር ፡ በዓይኖቼ ፡ እስከማይ አልዛቤል ፡ ምድሩን ፡ ሃገሩን ፡ ገዝታ ምን ፡ ሰላም ፡ አለ ፡ ለእኛ ፡ መኝታ እረፍት ፡ የለኝም ፡ ለሽፋሽፍቴ እስካያት ፡ ድረስ ፡ ወድቃ ፡ ከፊቴ ኧኸ ፡ ውሻ ፡ ሲበላት ኧኸ ፡ በዓይኔ ፡ አያለሁ የትናገረኝ ፡ ጌታ ፡ ታማኝ ፡ ነው (፪x) ና ፡ ውረድ ፡ ሲሉኝ (፫x) ስፍራው ፡ ተመችቶኝ ፡ እዛው ፡ ቀረሁኝ አልወርድም ፡ አልወርድም ፡ ተራራው ፡ ላይ የእግዚአብሔርን ፡ ክብር ፡ በዓይኖቼ ፡ እስከማይ ቤቱ ፡ በሸቀጥ ፡ ነጋዴ ፡ ሞልቶ አጠራው ፡ ጌታ ፡ ጅራፍን ፡ ሰርቶ ሁሉም ፡ ይሰግዳል ፡ ለአብ ፡ ክብር ቤቱ ፡ ሲጠራ ፡ የእግዚአብሔር ኧኸ ፡ የቤቱ ፡ ቅናት ኧኸ ፡ እኔን ፡ በልቶኛል ቤቱ ፡ ሲጠራ ፡ በዓይኔ ፡ ያሳየናል (፪x)