Loading
Singer
እስሬን ፡ ጥብቅ ፡ አደረገና ማረጂያውን ፡ ሳል ፡ አረገና ጉድጓድ ፡ ምሶ ፡ ሲጠብቀኝ ቀን ፡ ቀጥሮ ፡ ዋጥ ፡ ሊያደርገኝ ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ ያመለጠ (፬x) እስሬን ፡ ጥብቅ ፡ አደረገና ማረጂያውን ፡ ሳል ፡ አረገና ጉድጓድ ፡ ምሶ ፡ ሲጠብቀኝ ቀን ፡ ቀጥሮ ፡ ዋጥ ፡ ሊያደርገኝ ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ ያመለጠ (፬x) አዝ፦ ያን ፡ ለት ፡ ነው ፡ አድራሻዬ ፡ የተቀየረዉ ያን ፡ ለት ፡ ነው ፡ ችግር ፡ ለቆኝ ፡ ትቶኝ : የሄደው ያን ፡ ለት ፡ ነው ፡ ያ ፡ ከሳሼ ፡ ጉድ ፡ የፈላበት ያን ፡ ለት ፡ ነው ፡ ደጉ ፡ ጌታ ፡ ቤት ፡ የገባበት ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ ያመለጠ (፬x) ከሲኦል ፡ መትረፌ ፡ በኢየሱስ ፡ ማረፌ ፡ ይህ ፡ ካልገረመኝ ከልዑሉ ፡ ጋራ ፡ በቀኝ ፡ መቀመጤ ፡ ካላስጨፈረኝ ታዲያ ፡ ምን ፡ ይግረመኝ ፡ ከመትረፌ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ ያስጨፍረኝ ደሙን ፡ ከፍሎ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የሕይወቴ ፡ ጌታ ፡ ኧረፍት ፡ የሰጠኝ አዝ፦ ዛሬም ፡ ይግረመኝ ፡ እንጂ ፡ ነገም ፡ ይግረመኝ በእርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ ችግሬ/ጨለማው ፡ እጁን ፡ ያሰጠኝ (፪x) ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ ያመለጠ (፬x) ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ (፬x) በጣም ፡ ደካማ ፡ ሰው ፡ ሸክም ፡ ያጐበጠኝ ፡ የከበደብኝ እንዲያው ፡ ወዶኝ ፡ እንጂ ፡ መዳን ፡ ያልተገባኝ ፡ ሙት ፡ ሰው ፡ ነበርኩኝ መች ፡ ምህረት ፡ ወድጄ ፡ ወይስ ፡ እሮጬ ፡ ነው ፡ ይህ ፡ የሆነልኝ የቀደሰኝ ፡ ጌታ ፡ መርገሜን ፡ ሻረና ፡ በሕይወት ፡ ኑሪ ፡ አለኝ አዝ፦ ዛሬም ፡ ይግረመኝ ፡ እንጂ ፡ ነገም ፡ ይግረመኝ በእርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ ችግሬ/ጨለማው ፡ እጁን ፡ ያሰጠኝ (፪x) ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ ያመለጠ (፬x) እኔ ፡ ነኝ (፬x) ዘንዶ ፡ የተወጋልኝ ፡ እሳቱ ፡ የጠፋልኝ ከአፈር ፡ የተነሳሁኝ ፡ ጌታ ፡ ሞገስ ፡ የሆነኝ ዘንዶ ፡ የተወጋልኝ ፡ እሳቱ ፡ የጠፋልኝ ከአፈር ፡ የተነሳሁኝ ፡ ጌታ ፡ ሞገስ ፡ የሆነኝ አዝ፦ ያመለጠ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ ያመለጠ (፬x)