Loading
Singer
የተደረገልኝን ፡ አይቼ ከአንተ ፡ የተቀበልኩትን ፡ አይቼ በፊትህ ፡ ቅኔን ፡ ተቀኘሁኝ እንዲህ ፡ አልኩኝ አንተ ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ አንተ ኧረ ፡ አንተ ፡ ንጉሤ ፡ ነህ ፡ አንተ አንተ ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ አንተ ኧረ ፡ አንተ ፡ አባቴ ፡ ነህ ፡ አንተ ያላየሁት ፡ ዓለም ፡ ያልቀመስኩት ፡ ኑሮ በጌታ ፡ ሆነልኝ ፡ ይገርማል ፡ ዘንድሮ ተመስገን ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ ይባላል የአምላኬ ፡ ቅናት ፡ ይህንን ፡ አድርጓል ተመስገን ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ ይባላል የአምላኬ ፡ ቅናት ፡ ይህንን ፡ አድርጓል (፪x) እንዲህ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሲረዳ እንዲህ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ሲያሳርፍ (እንዲህ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሲረዳ እንዲህ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ሲያሳርፍ) (፪x) ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ ጌታን ፡ አመልካለሁ ጌታን ፡ አከብራለሁ (፪x) እርሱ ፡ የእኔ ፡ አባት ፡ መድሃኒቴ ፡ ነው (፫x) አቅም ፡ ብርቱ ፡ ሳለ ፡ ጉልበቴ ፡ ሳይደክም ለዚህ ፡ ከንቱ ፡ ዓለም ፡ ልቤን ፡ አላዝልም አቅም ፡ ብርቱ ፡ ሳለ ፡ ጉልበቴ ፡ ሳይደክም ለዚህ ፡ ከንቱ ፡ ዓለም ፡ ልቤን ፡ አላዝልም (፪x) እንደምን ፡ ይቻላል ፡ ያለ ፡ ጌታ ፡ ሆኖ በራስ ፡ መተማመን ፡ ድጋፍ ፡ ተሸፍኖ ዓለምን ፡ ናቅ ፡ አድርጐ ፡ ጌታን ፡ መወዳጀት ይህ ፡ ታላቅ ፡ ጥበብ ፡ ነው ፡ የሠማይ ፡ በረከት ዓለምን ፡ ናቅ ፡ አድርጐ ፡ ጌታን ፡ መወዳጀት ይህ ፡ ታላቅ ፡ ጥበብ ፡ ነው ፡ የሠማይ ፡ በረከት (፪x) እንዲህ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሲረዳ እንዲህ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ሲያሳርፍ (እንዲህ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሲረዳ እንዲህ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ሲያሳርፍ) (፫x)