Loading
Singer
አዝ፦ ያላንተ ፡ ኑሮ ፡ አይሆንልኝም ፡ ጌታዬ ፡ አይሆንልኝም እኔስ ፡ ያላንተ ፡ አይሆንልኝም ፡ ጌታዬ ፡ አይሆንልኝም ወጣሁ ፡ ወረድኩ ፡ ብዙ ፡ አየሁኝ እንዳንተ ፡ የሚሆን ፡ መቼ ፡ አገኘሁኝ ድካሜ ፡ ሁሉ ፡ ከንቱ ፡ ነበረ አንተ ፡ ስትመጣ ፡ ሕይወቴ ፡ አማረ አዝ፦ ታዲያ ፡ ያላንተ ፡ እንዴት ፡ አድርጌ ፡ እኖራለሁ ፡ እንዴት ፡ አድርጌ ያላንተ ፡ ኑሮ ፡ አይሆንልኝም ፡ ጌታዬ ፡ አይሆንልኝም የዓለም ፡ ፍቅር ፡ ተሟጦ ፡ ያልቃል ያንተ ፡ ፍቅር ፡ ግን ፡ መቼ ፡ ያረጃል አትጠገብም ፡ ቀርቦ ፡ ላየህ አቤት ፡ ጌታዬ ፡ ምን ፡ አይነት ፡ ነህ አዝ፦ ታዲያ ፡ ያላንተ ፡ እንዴት ፡ አድርጌ ፡ እኖራለሁ ፡ እንዴት ፡ አድርጌ ያላንተ ፡ ኑሮ ፡ አይሆንልኝም ፡ ጌታዬ ፡ አይሆንልኝም የአሕዛብ ፡ ኑሮ ፡ ሁሌ ፡ ይደንቀኛል ሰው ፡ ካለ ፡ ኢየሱስ ፡ እንዴት ፡ ይኖራል አንተን ፡ ያጣ ፡ ሰው ፡ ያልታደለ ፡ ነው ከርታታ ፡ መና ፡ ተስፋ ፡ የሌለው አዝ፦ እኔስ ፡ ኑሮ ፡ አይሆንልኝም ፡ ጌታዬ ፡ አይሆንልኝም እኔስ ፡ ያላንተ ፡ አይሆንልኝም ፡ ኢየሱስ ፡ አይሆንልኝም