Loading
Singer
አዝ፦ ወጥመዱ ፡ ተሰብሮ ፡ አመለጥኩኝ በአምላኬ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ አደርኩኝ እግዚአብሔር ፡ ጋሻ ፡ ሆኖልኛል እንግዲህ ፡ ማን ፡ ይቃወመኛል (፪x) እንግዲህስ ፡ ማን ፡ ይቃወመኛል (፬x) ጠላቴ ፡ ሊያጠፋኝ ፡ ሲሸምቅ የወደኩ ፡ መስሎት ፡ በእኔ ፡ ሊስቅ ነጋሪት ፡ ሲመታ ፡ ሲያስመታ እምነቴን ፡ ጉልበቴን ፡ ሊፈታ ቀና ፡ ብዬ ፡ ባላይ ፡ ኖሮ ፡ ዓይኖቸን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አንስቼ በጠፋሁ ፡ ነበር ፡ አስካሁን ፡ በሰልፉ ፡ ብዛት ፡ ፈርቼ ደካማን ፡ የምትረዳ ፡ አምላክ ፡ አኔን ፡ ደርሰህ ፡ እረዳኸኝ መከራዬን ፡ አሳለፍከው ፡ በኮረብታው ፡ ላይ ፡ አቆምከኝ አዝ፦ ወጥመዱ ፡ ተሰብሮ ፡ አመለጥኩኝ በአምላኬ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ አደርኩኝ እግዚአብሔር ፡ ጋሻ ፡ ሆኖልኛል እንግዲህ ፡ ማን ፡ ይቃወመኛል (፪x) እንግዲህስ ፡ ማን ፡ ይቃወመኛል (፬x) ጠንክሮ ፡ ብዙ ፡ የፈተነኝ ፡ የማይገፋ ፡ የመሰለኝ ወደቀ ፡ እንደ ፡ ቀላል ፡ ዕቃ ፡ ሰማሁት ፡ ድንፋታው ፡ ሲያበቃ ቀና ፡ ብዬ ፡ ስመለከት ፡ ከመከራዬ ፡ ቀን ፡ በላይ ለካስ ፡ ጌታ ፡ አስቦልኝ ፡ ቤቴን ፡ በበረከት ፡ ሊሞላ ሸሸገኝ ፡ ከጉያው ፡ ገባሁ ፡ ከጥላው ፡ ሥር ፡ አሳደረኝ እዘምራለሁ ፡ ለሥሙ ፡ በቤቱ ፡ ስለተመቸኝ አዝ፦ ወጥመዱ ፡ ተሰብሮ ፡ አመለጥኩኝ በአምላኬ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ አደርኩኝ እግዚአብሔር ፡ ጋሻ ፡ ሆኖልኛል እንግዲህ ፡ ማን ፡ ይቃወመኛል (፪x) እንግዲህስ ፡ ማን ፡ ይቃወመኛል (፬x) ኃይሌ ፡ ነው ፡ እታመነዋለሁ ፡ ክብሬ ፡ ነው ፡ እደገፈዋለሁ ሞገሴ ፡ የማያሳፍረኝ ፡ በፀጋው ፡ የሚደጋግፈኝ መከታዬ ፡ ነው ፡ ጋሻዬ ፡ ሥሙን ፡ በእውነት ፡ እጠራዋለሁ ስንቱን ፡ ሸለቆ ፡ ተራራ ፡ ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ አልፌአለሁ ከጐኔ ፡ የሚቆም ፡ ዘለዓለም ፡ እንዴ ፡ እንኳን ፡ አላሳፈረኝ በአምላኬ ፡ ቀን ፡ ወጥቶልኛል ፡ እንግዲህ ፡ ማን ፡ ሊቃወመኝ አዝ፦ ወጥመዱ ፡ ተሰብሮ ፡ አመለጥኩኝ በአምላኬ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ አደርኩኝ እግዚአብሔር ፡ ጋሻ ፡ ሆኖልኛል እንግዲህ ፡ ማን ፡ ይቃወመኛል (፪x) እንግዲህስ ፡ ማን ፡ ይቃወመኛል (፰x)