Loading
Singer
በአፍላ ፡ ልጅነት ፡ እራዕይ ፡ ሰጥቶኝ ውስጤ ፡ እይፈላ ፡ እንዴት ፡ ያስችለኝ በዚህ ፡ ደስ ፡ ብሎኝ ፡ ብሰብክ ፡ ባወራ መንገድ ፡ ዘጋብኝ ፡ ያባላጋራ በአጭር ፡ ቀጨሁት ፡ ብሎ ፡ ሲዝናና ጥሼው ፡ መሄዴን ፡ አላየምና ተጥዬ ፡ የምቀር ፡ መስሎታልና እንዲህ ፡ የዋዛ ፡ መቼ ፡ ሆንኩና መስሎት ፡ የፈራሁ ፡ ገና ፡ ለገና ጉዱ ፡ ፈላበት ፡ ነካካኝና አዝ፦ ወረደ ፡ አምላኬ ፡ ከሃያላን ፡ ጋራ ከሰማይ ፡ መቅደሱ ፡ አያበራ ወረደ ፡ አምላኬ ፡ ከሃያላኑ ፡ ጋር በሰልፉ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ሊዋጋ አልመለስም ፡ ሰልፉን ፡ ፈርቼ ፤ አልመለስም ፡ ቅባቱን ፡ ይዤ አልመለሰም ፡ አምላኬን ፡ ይዤ ፣ አልመለስም ፡ ቅባቱን ፡ ይዤ አልመለስም ፡ ሰልፉን ፡ ፈርቼ ፤ አልመለስም ፡ ቅባቱን ፡ ይዤ ምንም ፡ ቢያወራ ፡ እኔ ፡ ላልፈራ አታመልጠኝም ፡ ቢል ፡ ለፉከራ ዛቻ ፡ ፉከራ ፡ ላይሆን ፡ ላይሰራ ጸጉሬን ፡ ዐይነካም ፡ ምን ፡ ቢንጠራራ ዝምበል ፡ ጠላቴ ፡ እስኪ ፡ አትፎክር ከአንተ ፡ የሚበልጥ ፡ አለኝ ፡ እግዚአብሔር ሰልፉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ መሆኑን ፡ ሳያውቅ ዘሎ ፡ ገባበት ፡ አቤት ፡ መናናቅ ወይ ፡ አለማሰብ ፡ አዬ ፡ መሳሳት መቼ ፡ ይሆናል ፡ በእሳት ፡ መጫወት አዝ፦ ወረደ ፡ አምላኬ ፡ ከሃያላን ፡ ጋራ ከሰማይ ፡ መቅደሱ ፡ አያበራ ወረደ ፡ አምላኬ ፡ ከሃያላኑ ፡ ጋር በሰልፉ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ሊዋጋ አልመለስም ፡ ሰልፉን ፡ ፈርቼ ፤ አልመለስም ፡ ቅባቱን ፡ ይዤ አልመለሰም ፡ አምላኬን ፡ ይዤ ፣ አልመለስም ፡ ቅባቱን ፡ ይዤ አልመለስም ፡ ሰልፉን ፡ ፈርቼ ፤ አልመለስም ፡ ቅባቱን ፡ ይዤ ጠላቴ ፡ ሲያየኝ ፡ መስሎት ፡ ማልበቃ ጌታ ፡ ግን ፡ ቀባኝ ፡ አድርጐ ፡ አለቃ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ሲያየኝ ፡ አንተ ፡ ብላቴና አትችለውም ፡ ህጻን ፡ ነህና ህጻን ፡ ብመስልም ፡ ምንም ፡ ማልረባ ገልብጬው ፡ መጣሁ ፡ ያንን ፡ ገለባ ሲያስብ ፡ ጠላቴ ፡ በአምላኬ ፡ ማፍር እኔ ፡ ሳለቅስ ፡ እርሱ ፡ ሊፎክር ተአምር ፡ ሰራና ፡ የእኔ ፡ እግዚአብሔር ከዐይኔ ፡ አስወገደው ፡ እስኪ ፡ ልዘምር አዝ፦ ወረደ ፡ አምላኬ ፡ ከሃያላን ፡ ጋራ ከሰማይ ፡ መቅደሱ ፡ አያበራ ወረደ ፡ አምላኬ ፡ ከሃያላኑ ፡ ጋር በሰልፉ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ሊዋጋ አልመለስም ፡ ሰልፉን ፡ ፈርቼ ፤ አልመለስም ፡ ቅባቱን ፡ ይዤ አልመለሰም ፡ አምላኬን ፡ ይዤ ፣ አልመለስም ፡ ቅባቱን ፡ ይዤ አልመለስም ፡ ሰልፉን ፡ ፈርቼ ፤ አልመለስም ፡ ቅባቱን ፡ ይዤ