Loading
ይህን ፡ ነገር ፡ ለዓለም ፡ ቅዱሱ ፡ መጽሃፍ ከዳር ፡ ዳር ፡ ሰማሁ ፡ እውነቱ ፡ አይታለፍ ዘር ፡ ቀለም ፡ ላይለየው ፡ ለሁሉም ፡ ተፈቅዷል ለወደዱት ፡ ሁሉ ፡ ሰላምን ፡ ይሰጣል አዝ:- ወንጌል ፡ መሪ ፡ ወንጌል ፡ ሰላም ለሰው ፡ ልጆች ፡ ይሁን ፡ መዳን ለህዝባችን ፡ ይሁን ፡ መዳን (፪x) የታሰሩ ፡ ይፈታሉ ፡ የታመሙት ፡ ይድናሉ ይፈታሉ ፡ ይድናሉ ፡ ፈውስ ፡ ነው ፡ ወንጌሉ (ኡዎዉዎዎ) ፈውስ ፡ ነው ፡ ወንጌሉ ፡ ፈውስ ፡ ነው ፡ ወንጌሉ (፪x) ሊታረም ፡ የማይችል ፡ ፍፁም ፡ እውነት ፡ አለው ሊሽረው ፡ የቆመ ፡ የትኛው ፡ ጠቢብ ፡ ነው የጠቢባን ፡ ጠቢብ ፡ ይህን ፡ ከገለጸው የደህንነት ፡ መንገድ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው አዝ:- ወንጌል ፡ መሪ ፡ ወንጌል ፡ ሰላም ለሰው ፡ ልጆች ፡ ይሁን ፡ መዳን ለህዝባችን ፡ ይሁን ፡ መዳን (፪x) የታሰሩ ፡ ይፈታሉ ፡ የታመሙት ፡ ይድናሉ ይፈታሉ ፡ ይድናሉ ፡ ፈውስ ፡ ነው ፡ ወንጌሉ (ኡዎዉዎዎ) ፈውስ ፡ ነው ፡ ወንጌሉ ፡ ፈውስ ፡ ነው ፡ ወንጌሉ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.