Loading
Singer
እንደኔ ፡ ማነው ፡ የእኔስ ፡ ልዩ ፡ ነው ወደቀ ፡ ሲባል ፡ ጌታ ፡ የሚያነሳው ኢየሱስ ፡ ረድቶኛል ፡ በሁሉ ፡ አብልጦ ከፍቶ ፡ አዲስ ፡ ምዕራፍ ፡ ታሪክ ፡ ለውጦ አዝ፦ ውለታው ፡ በዛ ፡ ጌታ ፡ ውለታው ፡ በዛ ውለታው ፡ በዛ ፡ ኢየሱስ ፡ ውለታው ፡ በዛ (፪x) አቤት ፡ እንደኔ ፡ ማንን ፡ ረዳህ አቤት ፡ እንደኔ ፡ ማንን ፡ አገዝክ አቤት ፡ ምህረትህ ፡ የገነነለት አቤት ፡ እንደኔስ ፡ ማን ፡ በዛለት አዝ፦ ውለታው ፡ በዛ ፡ ጌታ ፡ ውለታው ፡ በዛ ውለታው ፡ በዛ ፡ ኢየሱስ ፡ ውለታው ፡ በዛ (፪x) አስታውሳለሁ ፡ ከምን ፡ እንዳነሳኝ ሁሉም ፡ ሲጠየፍ ፡ እያየ ፡ ሲያልፈኝ ቁስሌን ፡ ጠራርጐ ፡ እምባዬን ፡ ሲያብስ አስቦ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ እዚህ ፡ እንድደርስ አዝ፦ ውለታው ፡ በዛ ፡ ጌታ ፡ ውለታው ፡ በዛ ውለታው ፡ በዛ ፡ ኢየሱስ ፡ ውለታው ፡ በዛ (፪x) አቤት ፡ እንደኔ ፡ ማንን ፡ ረዳህ አቤት ፡ እንደኔ ፡ ማንን ፡ አገዝክ ፡ (አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት) አቤት ፡ ምህረትህ ፡ የገነነለት አቤት ፡ እንደኔስ ፡ ማን ፡ በዛለት አዝ፦ ውለታው ፡ በዛ ፡ ጌታ ፡ ውለታው ፡ በዛ ፡ (ውለታው) ውለታው ፡ በዛ ፡ ኢየሱስ ፡ ውለታው ፡ በዛ (፪x) ክብሬ ፡ ትዘምር ፡ ዝምም ፡ አትበል ለቅሶዬን ፡ ለደስታ ፡ ጌታ ፡ ለውጧል ማቄንም ፡ ቀዶ ፡ ደስታ ፡ አስታጠቀኝ ምህረቱ ፡ በዝቶ ፡ በፊቱ ፡ አቆመኝ ምህረቱ ፡ በዛ ፡ ጌታ ፡ ምህረቱ ፡ በዛ ምህረቱ ፡ በዛ ፡ ኢየሱስ ፡ ምህረቱ ፡ በዛ ጥበቃው ፡ በዛ ፡ ጌታ ፡ ጥበቃው ፡ በዛ ጥበቃው ፡ በዛ ፡ ጌታ ፡ ጥበቃው ፡ በዛ ሰላሙ ፡ በዛ ፡ ጌታ ፡ ሰላሙ ፡ በዛ ሰላሙ ፡ በዛ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰላሙ ፡ በዛ