Loading
Singer
ውለታው ፡ አምላኬ ፡ ለኔ ፡ ያደረገው አያልቅም ፡ ባወራው ፡ ከእምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ተመስገን ፡ ልበለው በምድር ፡ ላለው ፡ ለእንዳዱ ፡ ሰው ፡ ግድ ፡ የተሰኘው ራሱን ፡ ለዓለም ፡ ቤዛ ፡ አድርጐ ፡ እንዲሁ ፡ የሰጠው ለጠሉትና ፡ ላልተቀበሉት ፡ ሆኖ ፡ መስቀል ፡ ላይ የሚያደርጉትን ፡ አያውቁምና ፡ ይቀር ፡ በል ፡ አባት ፡ ሆይ ያለው ፡ ይሄ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ ዓይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው ምንስ ፡ ዓይነት ፡ ቋንቋ ፡ ይችላል ፡ ሊገልጸው በምድር ፡ ካሉ ፡ ከተዋረዱ ፡ ከድሆች ፡ በላይ ኢየሱስ ፡ ስለእኛ ፡ ቤዛ ፡ ሆነልን ፡ መጥቶ ፡ ከሰማይ የሁላችንን ፡ በደልና ፡ ኃጢአት ፡ ተሸከመልን እዳችንን ፡ እርሱ ፡ ከፍለ ፡ ነጻም ፡ አወጣን በፍፁም ፡ ልባችን ፡ ጌታን ፡ ብንወደው አይገባውም ፡ ወይ ፡ ለእኛ ፡ ላደረገው መች ፡ በዚህ ፡ ብቻ ፡ በዚህ ፡ አበቃ ፡ የኢየሱስ ፡ ፍቅር ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ወራስህ ፡ አረገን ፡ አብሮን ፡ የምኖር የእርሱ ፡ የሆነውን ፡ አንዳችም ፡ ሳይቀር ፡ ለእኛ ፡ ሰጠው ባርኮቱን ፡ ሁሉ ፡ ምንም ፡ ሳይሰስት ፡ ለእኛ ፡ አፈሰሰው ታዲያ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ለእርሱ ፡ ብኖርለት ይገባዋል ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በዛበት ይህንን ፡ ውለታ ፡ የዋልልን ፡ ፡ ኢየሱስ ፡ ይመጣል በዚህች ፡ ምድር ፡ ላይ ፡ ናፍቀን ፡ እንቀርም ፡ መጥቶ ፡ ይወስደናል ወዳችንን ፡ በዓይናችን ፡ እናዋለን ፡ ወድቀን ፡ ከእግሩ ፡ ስር ፡ እንወድሃለን ፡ እንለዋለን ፡ ከተስፋ ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ የተባረከው ፡ ተስፋችን ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ስናየው ፡ ባይናችን