Loading
Singer
ይመለክ ፡ ይመለክ ፡ ወጉ ፡ ነው ፡ ይመለክ ይመለክ ፡ ይመለክ ፡ ደንቡ ፡ ነው ፡ ይመለክ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ኧረ ፡ ማነው? አምሳያ ፣ ወደር ፣ እኩያ ፡ የሌለው! የምድርን ፡ መሠረት ፡ ያጸና መስፈሪያ ፡ መለኪያዋን ፡ የዘረጋ ከእግዚአብሕዔር ፡ ሌላ ፡ ኧረ ፡ ማነው? ሊመለክ ፡ ሊከበር ፡ የሚገባው! በላይ ፡ በላይ ፡ ላብዛው ፡ ምሥጋናውን በላይ ፡ በላይ ፡ ላብዛው ፡ ዝማሬውን በላይ ፡ በላይ ፡ ላብዛው ፡ አምልኮውን እጅጉን ፡ የከበረውን ፡ የከበረውን መልሼ ፡ አከብረዋለሁን ፡ አከብረዋለሁኝ እጅጉን ፡ የገነነውን ፡ የገነነውን! መልሼ ፡ አገነዋለሁኝ ፡ አገነዋለሁኝ! ይመለክ ፡ ይመለክ ፡ ወጉ ፡ ነው ፡ ይመለክ ይመለክ ፡ ይመለክ ፡ ደንቡ ፡ ነው ፡ ይመለክ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ኧረ ፡ ማነው? አምሳያ ፣ ወደር ፣ እኩያ ፡ የሌለው! ሰማይ ፡ ዙፋንህ ፡ ነው ፡ የጸና ምድር ፡ ደግሞ ፡ የእግርህ ፡ መረገጫ በዓይነቱ ፡ በፍጥረቱ ፡ የሚያስደንቅ እግዚአብሔር ፡ ሆነብኝ ፡ ለእኔስ ፡ ትልቅ ይመለክ ፡ ይመለክ ፡ ወጉ ፡ ነው ፡ ይመለክ ይመለክ ፡ ይመለክ ፡ ደንቡ ፡ ነው ፡ ይመለክ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ኧረ ፡ ማነው? አምሳያ ፣ ወደር ፣ እኩያ ፡ የሌለው! ብቻውን ፡ አዛዥ ፡ ነው ፡ አጋዥ ፡ ሳይሻ ትዕዛዙንስ ፡ የሚሽር ፡ የቱ ፡ ጀግና ? ያለ ፡ ተቀናቃኝ ፡ ሁሉን ፡ የሚገዛ አልፋና ፡ ዖሜጋ ፡ ነው ፡ ጌታ ! በላይ ፡ በላይ ፡ ላብዛው ፡ ምሥጋናውን በላይ ፡ በላይ ፡ ላብዛው ፡ ዝማሬውን በላይ ፡ በላይ ፡ ላብዛው ፡ አምልኮውን እጅጉን ፡ የከበረውን ፡ የከበረውን መልሼ ፡ አከብረዋለሁን ፡ አከብረዋለሁኝ እጅጉን ፡ የገነነውን ፡ የገነነውን ! መልሼ ፡ አገነዋለሁኝ ፡ አገነዋለሁኝ ! ይመለክ ፡ ይመለክ ፡ ወጉ ፡ ነው ፡ ይመለክ ይመለክ ፡ ይመለክ ፡ ደንቡ ፡ ነው ፡ ይመለክ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ኧረ ፡ ማነው? አምሳያ ፣ ወደር ፣ እኩያ ፡ የሌለው!