Loading
Singer
ቸርነቱን ፡ ለእኔ ፡ ሁሌ ፡ እዘምራለሁ የአባትነት ፡ ፍቅሩን ፡ ቀምሼ ፡ ስላየሁ ጐልጐታ ፡ አናት ፡ ላይ ፡ ለእኔ ፡ ሞቶልኛል የኀጢአት ፡ እስራቴን ፡ በጥሶ ፡ ጥሎታል (፪x) አዝ፦ ወዶኛልና ፡ አዳነኝ (፪x) ምህረቱ ፡ ሰው ፡ አደረገኝ (፫x) ወዶኛልና ፡ አዳነኝ (፪x) ምህረቱ ፡ ሰው ፡ አደረገኝ (፫x) ከሰማይ ፡ ሰማያት ፡ ከዙፋኑ ፡ ወርዶ ሁሉን ፡ ስለፍቅር ፡ አደረገ ፡ ባዶ መስቀል ፡ ተሸክሞ ፡ ደፋ ፡ ቀና ፡ ያለው ያ ፡ ሁሉ ፡ ስቃዩ ፡ ለእኔ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ነው (፪x) አዝ፦ ወዶኛልና ፡ አዳነኝ (፪x) ምህረቱ ፡ ሰው ፡ አደረገኝ (፫x) አደባባይ ፡ ቆመ ፡ እርቃኑን ፡ ስለ ፡ እኔ አላፈረብኝም ፡ ኢየሱስ ፡ መድኅኔ በእኔ ፡ ፈንታ ፡ ሞቶ ፡ እኔን ፡ አድኖኛል በከበረው ፡ ደሙ ፡ ጌታዬ ፡ ዋጅቶኛል (፪x) አዝ፦ ወዶኛልና ፡ አዳነኝ (፪x) ምህረቱ ፡ ሰው ፡ አደረገኝ (፫x) የምህረት ፡ መግቢያ ፡ በሩ ፡ ተክፈተ የጥሉ ፡ ግድግዳ ፡ በደሙ ፡ ፈረሰ ተፈጸመ ፡ ብሎ ፡ ሁሉን ፡ ጨርሶታል ሞትና ፡ ሲዖልን ፡ ድል ፡ ነስቶ ፡ ተነስቷል (፪x) አዝ፦ ወዶኛልና ፡ አዳነኝ (፪x) ምህረቱ ፡ ሰው ፡ አደረገኝ (፮x)