Loading
Singer
ዙፋኑን ፡ ትቶ ፡ ወረደ ፈልጐ ፡ እኔን ፡ ሊያገኘኝ ሳልወደው ፡ ቀድሞ ፡ ወደደኝ ከዓለም ፡ ለይቶ ፡ መረጠኝ በውርደት ፡ ሞትን ፡ ከመሞት ፍቅሩን ፡ ለእኔ ፡ ገለጠልኝ ከዘለዓለም ፡ ፍቅር ፡ ስቦ ወደ ፡ እልፍኙ ፡ አስገባኝ አዝ፦ ውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x) ከእልፍ ፡ የተመረጠ ፡ ነው ፍቅሩ ፡ ለዘላዓለም ፡ ነው ወዶኛል ፡ ወድጄዋለሁ እንደርሱ ፡ የታለ ፡ ማነው (፪x) ማንም ፡ መጥቶ ፡ አይነጥለኝ አንዴ ፡ የእራሱ ፡ አድርጐኛል ይተወኛል ፡ ብዬ ፡ አልፈራም የከሳሼን ፡ ወሬ ፡ አልሰማም ወረተኛ ፡ አይደል ፡ እንደሰው ፡ ለዘለዓለም ፡ ወዶኛል ጥፋት ፡ እንኳን ፡ ሲያገኝብኝ ፡ በፍቅር ፡ መክሮ ፡ ያድነኛል አዝ፦ ውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x) ከእልፍ ፡ የተመረጠ ፡ ነው ፍቅሩ ፡ ለዘላዓለም ፡ ነው ወዶኛል ፡ ወድጄዋለሁ እንደርሱ ፡ የታለ ፡ ማነው (፪x) ግርማው ፡ በቃል ፡ አይገለጽ ፊቱ ፡ እንደፀሐይ ፡ ሲያበራ ከእኔ ፡ ወዳጅ ፡ አይበልጥም ማንም ፡ በምንም ፡ ቢጠራ በእርሱ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ሁልጊዜ ፡ ሃሴት ፡ አደርጋለሁ ኩራት ፡ ኩራት ፡ ይሰማኛል የእርሱ ፡ መሆኔ ፡ አርክቶኛል አዝ፦ ውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x) ከእልፍ ፡ የተመረጠ ፡ ነው ፍቅሩ ፡ ለዘላዓለም ፡ ነው ወዶኛል ፡ ወድጄዋለሁ እንደርሱ ፡ የታለ ፡ ማነው (፪x) ይታወቅ ፡ በምድር ፡ ሁሉ እኔ ፡ ኢየሱስን ፡ መውደዴ ያኮራል ፡ ያስመካል ፡ እንጂ አያሳፍረኝም ፡ ውዴ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ የምሆንበት የሠርጌን ፡ ቀን ፡ ናፍቄያለሁ ነፍሴን ፡ በደሙ ፡ አንጽቼ ምጻቱን ፡ እጠብቃለሁ አዝ፦ ውዴ (፫x) ፡ ኢየሱስ (፫x) ከእልፍ ፡ የተመረጠ ፡ ነው ፍቅሩ ፡ ለዘላዓለም ፡ ነው ወዶኛል ፡ ወድጄዋለሁ እንደርሱ ፡ የታለ ፡ ማነው (፪x)