Loading
Singer
ከተሸሸኩበት ፡ መንደሬ መጣ ፡ ኢየሱስ ፡ ገባ ፡ ሰፈሬ ጠራኝ ፡ ቀርቦ ፡ በቁልምጫው ሊያስገባኝ ፡ ወደ ፡ ጉያው የወዳጄ ፡ የአምላኬ ጥሪው ፡ ደርሶኛል ምን ፡ አደርጋለሁ ቀሪው ፡ ዘመኔን ፡ ሰጥቼዋለሁ ይስራበት ፡ ይክበርበት ያለው ፡ አላማ ፡ ፈቃድ ፡ ሀሳቡ ይጠቅለል ፡ በእኔ ፡ ይድረስ ፡ ከግቡ ሲጠራኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ) ሲለየኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ) ሲቀባኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ) ሲመርጠኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ) (፪x) መገለጫው ፡ ነው ፡ መገለጫው ለሰማይ ፡ ወኪል ፡ የምድር ፡ ጨው የምድርን ፡ ክፋት መርገም ፡ ሰባሪ የሰላም ፡ ዘማች ፡ ለሰማይ ፡ ጥሪ (፪x) ሲጠራኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ) ሲለየኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ) ሲቀባኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ) ሲመርጠኝ (ክብር ፡ አይቶልኝ (፪x) ማያንገራግረው ፡ ማያመቻምቸው ትዳር ፡ ባለበት ፡ ሰፈር ራሱን ፡ የማይጠምደው ጠሪውን ፡ ሲያስደስተው ሲገኝ ፡ በጸና ፡ እምነቱ ማረጉ ፡ ነው ፡ በላዩ ሚታየው ፡ ሽልማቱ (፪x) ወዶ ፡ ዘማች ፡ ወዶ ፡ ዘማች ለወንጌሉ ፡ ወዶ ፡ ዘማች ፈቅዶ ፡ ዘማች ፡ ፈቅዶ ፡ ዘማች ለዚህ ፡ ጥሪ ፡ ፈቅዶ ፡ ዘማች ማነው (ወዶ ፡ ዘማች) ማነው (ለዚህ ፡ ጥሪ) ማነው (ራሱን ፡ ሰቶ) ማነው (ጌታውን ፡ አስጠሪ) ማነው (እኔ ፡ ነኝ) ማነው (እኔ ፡ ነኝ) ማነው (እኔ ፡ ነኛ) ማነው (ለወንጌሉ) ማነው (ዘማች ፡ አርበኛ) ማነው (፬x) ማነው