Loading
Singer
ልቤ ፡ ዋተተ ፡ ዋተተ መንፈሴም ፡ ታወከብኝ ልጄ ፡ አንተን ፡ አጥቼ ፡ ከጉያዬ እንዴት ፡ ልረፍ ፡ በምን ፡ anjet chye እህ ፡ እህህህህ እህህ ፡ ሆነብኝ ፡ ጠዋት ፡ ማታ ወንድሞችህ ፡ ቢኖሩም ፡ በቤት አይተኩትም ፡ ለአንተ ፡ ያለኝን ፡ ቦታ አዝ፦ ወዴት ፡ አለህ ድምጼን ፡ ሰምተህ ፡ አለሁ ፡ በለኛ ፈጠን ፡ ብለህ ፡ ወደ ፡ እቅፌ ፡ ግባ (፪x) ደጅ/በር ፡ አፍ ፡ ላይ ፡ ቆሞ ፡ ያንኳኳል ፡ ወዳጅ ይጣራል ፡ ወዳጅ (፪x) ድምጹን ፡ ሲያሰማ ፡ አስገባው ፡ ከፍተህ አይጥና ፡ ደጅ ፣ አይጥና ፡ ደጅ (፪x) እናት ፡ ትረሳ ፡ ይሆናል ፡ አምጣ ፡ የወለደችውን እኔማ ፡ እንዴት ፡ እንዴት ፡ ነው ፡ እንዴት አንተን ፡ ጥሎ ፡ መኖር ፡ በሞቀ ፡ ቤት ልጄን ፡ ካልያዝኩት ፡ አልረካ ክርትት ፡ አለ ፡ ዓይኔ ፡ አንተን ፡ ፍለጋ ወድሃለሁ ፡ ልጄ ፡ ናና ፡ ናና ሙሉ ፡ እንዲሆን ፡ የቤቴ ፡ ምሥጋና አዝ፦ ወዴት ፡ አለህ ድምጼን ፡ ሰምተህ ፡ አለሁ ፡ በለኛ ፈጠን ፡ ብለህ ፡ ወደ ፡ እቅፌ ፡ ግባ (፪x) ደጅ/በር ፡ አፍ ፡ ላይ ፡ ቆሞ ፡ ያንኳኳል ፡ ወዳጅ ይጣራል ፡ ወዳጅ (፪x) ድምጹን ፡ ሲያሰማ ፡ አስገባው ፡ ከፍተህ አይጥና ፡ ደጅ ፣ አይጥና ፡ ደጅ (፪x) አባ ፡ አባባ ፡ ስትለኝ እስቲ ፡ ልስማህ ፡ ያ ፡ ድምጽህ ፡ ናፈቀኝ ሸክምህን ፡ አውርድ ፡ ከጫንቃህ ላሳርፍህ ፡ አለሁ ፡ አባትህ የሚያሳየው ፡ ጐልጐታ ዛሬም ፡ ያው ፡ ነው ፡ ፍቅሬ ፡ መች ፡ ተገታ በላ ፡ እንሂድ ፡ ወደ ፡ ቤታችን እኔም ፡ ልረፍ ፡ አግኝቼ ፡ አንተን አዝ፦ ወዴት ፡ አለህ ድምጼን ፡ ሰምተህ ፡ አለሁ ፡ በለኛ ፈጠን ፡ ብለህ ፡ ወደ ፡ እቅፌ ፡ ግባ (ወዴት ፡ አለህ) ፡ ወዴት ፡ አለህ (ድምጼን ፡ ሰምተህ) ፡ ድምጼን ፡ ሰምተህ አለሁ ፡ በለኛ ፡ (አለሁ ፡ በለኛ) ፈጠን ፡ ብለህ ፡ ወደ ፡ እቅፌ ፡ ግባ (፪x)