Loading
Singer
አዝ፦ ምንም ፡ ቢባል ፡ ምንም (፬x) የሚመስለው ፡ የለም የትም ፡ ቢኬድ ፡ የትም (፬x) የሚተካው ፡ የለም ወደርሱ ፡ ቅረቡ ፡ ያበራላችኋል ወደርሱ ፡ ቅረቡ ፡ ፊታችሁ ፡ አያፍርም ቸር ፡ እንደሆነ ፡ ቅመሱ ፡ ኑ ከብዙ ፡ ፍቅሩ ፡ ልበሱ (፪x) አዝ፦ ምንም ፡ ቢባል ፡ ምንም (፬x) የሚመስለው ፡ የለም የትም ፡ ቢኬድ ፡ የትም (፬x) የሚተካው ፡ የለም በትንሽነቴ ፡ ያደመጠኝ ፡ ጌታ በትንሽነቴ ፡ ያናገረኝ ፡ ጌታ አልተወኝም ፡ በምንም ፡ ሁኔታ ልዩ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ አቤት ፡ የእኔ ፡ ጌታ አልጣለኝም ፡ በምንም ፡ ሁኔታ ታማኝ ፡ ነው ፡ አቤት ፡ የእኔ ፡ ጌታ እንደ ፡ አቤል ፡ መስዋዕት ፡ ይሂድ ፡ አምልኮዬ እንደ ፡ አቤል ፡ መስዋዕት ፡ ይድረስ ፡ ዝማሬዬ የልቤ ፡ ይድረስ ፡ ለልቤ ፡ ጌታዬ (፪x) ይኸው ፡ ዕልልታ ፡ ለኢየሱስ ፡ ጌታዬ (፪x) ይኸው ፡ ጭብጨባ ፡ ለኢየሱስ ፡ ጌታዬ (፪x) ከላይ ፡ አይደለም ፡ ከላይ ፡ ከላይ (፬x) ከልቤ ፡ የሆነው ፡ ይኸው ፡ ዝማሬዬ (፪x) ከውስጤ ፡ የሆነው ፡ ይኸው ፡ ዕልልታዬ (፪x) ይሂድ ፡ ይሂድ ፡ ይሂድ (፬x)