Loading
Singer
ወድጄ ፡ ፈቅጄ ፡ እኔ ፡ የማመልክህ የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ እግዚአብሔር ፡ ብርሃኔ ፡ መድኃኒቴ ፡ ሆነህ እዚህ ፡ የመድረሻ ፡ መታመኛዬ ፡ ነህ ሃ ፡ ሃሌሉያ (፬x) አንተን ፡ እያመለኩ ፡ ጉዞ ፡ ከጀመርኩኝ በትንሹ ፡ ዕድሜዬ ፡ ቤትህ ፡ ከመጣሁኝ ፍቅር ፡ እንጂ ፡ ከአንተ ፡ ክፉን ፡ አላየሁም ለማምለክ ፡ ፈቅጄ ፡ በዚህ ፡ ተረታሁኝ ተባረክ ፡ አሃሃ ተመስገን ፡ ኦሆሆ (፪x) በሕይወቴ ፡ ትልቅ ፡ ስፍራ የምሰጠው ፡ ለአንተ ፡ ነው በኑሮዬ ፡ ሰፊ ፡ ቦታ የምሰጠው ፡ ለአንተ ፡ ነው (፪x) ጌታዬ ፡ ለአንተ ፡ ነው አምላኬ ፡ ለአንተ ፡ ነው ንጉሤ ፡ ለአንተ ፡ ነው ሕይወቴ ፡ በአንተ ፡ ነው ሃ ፡ ሃሌሉያ (፬x) ፍቅር ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ፍቅር ፡ ነህ ፍቅር ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ ፡ ፍቅር ፡ ነህ (፪x) ሃ ፡ ሃሌሉያ (፬x)