Loading
Singer
የተወደዳችሁ ፡ አድማጮቼ ፣ ከዚህ ፡ ቀጥሎ ፡ የምታደምጡት ፡ መዝሙር ፡ በሉቃስ ፡ ወንጌል ፡ ምእራፍ ፡ ፲፭ ፡ ከቁጥር ፡ ፲፩ - ፳፬ ፡ ድረስ ፡ በተፃፈው ፡ የኮብላይ ፡ ልጅ ፡ ታሪክ ፡ የተወሰደ ፡ መሆኑን ፡ እያስታወስኩ ፡ በዚህ ፡ ታሪክ ፡ ምሳሌነት ፡ የእግዚአብሔር ን፡ አባታዊ ፡ እና ፡ ዘለዓለማዊ ፡ ፍቅር ፡ አሳስባችኋለሁ ። በምታደምጧቸው ፡ ዝማሬዎች ፡ ሁሉ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይባርካችሁ ። አሜን ። አዝ፦ ወደ ፡ አባቴ ፡ ወደ ፡ ቀድሞ ፡ ቤቴ ፡ እመለሳለሁ እንደ ፡ ልጁም ፡ ባይሆን ፡ እንደ ፡ ባሪያው ፡ እኖራለሁ (፪x) መስሎኝ ፡ ነበር ፡ እኔ ፡ እራሴን ፡ የገዛሁ ንብረቴን ፡ ሰብስቤ ፡ ሩቅ ፡ ሃገር ፡ ተነሳሁ ለካስ ፡ ልጅ ፡ ኖሬያለሁ ፡ ምራቄን ፡ ያልዋጥኩኝ ለወፍ ፡ ለአሞራ ፡ ያለኝን ፡ በተንኩኝ ጉልበቴም ፡ ደከመ ፡ ሕይወቴም ፡ ባከነ ለካስ ፡ አባት ፡ ኖሮዋል ፡ ጉዴን ፡ የሸፈነ አዝ፦ ወደ ፡ አባቴ ፡ ወደ ፡ ቀድሞ ፡ ቤቴ ፡ እመለሳለሁ እንደ ፡ ልጁም ፡ ባይሆን ፡ እንደ ፡ ባሪያው ፡ እኖራለሁ (፪x) ወዳጄ ፡ ነበረ ፡ ካለኝ ፡ ያካፈልኩት ያጣሁ ፡ የነጣሁ ፡ እለት ፡ ከቦታው ፡ አጣሁት ሁሉም ፡ በር ፡ ዘግቶ ፡ አላውቅህም ፡ አለኝ የሚያዝንልኝ ፡ አጣሁ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ አገለለኝ አየሁ ፡ ተገነዘብኩ ፡ ወዳጅ ፡ ማንነቱን ማን ፡ ይሆንለታል ፡ ለሰው ፡ እንደ ፡ አባቱ? አዝ፦ ወደ ፡ አባቴ ፡ ወደ ፡ ቀድሞ ፡ ቤቴ ፡ እመለሳለሁ እንደ ፡ ልጁም ፡ ባይሆን ፡ እንደ ፡ ባሪያው ፡ እኖራለሁ (፪x) ሰርቼ ፡ እንዳልበላ ፡ ጨርሶ ፡ የለኝ ፡ ሞያ ተደብቄ ፡ ኖርኩኝ ፡ በአባቴ ፡ ጉያ ጉዴ ፡ ተገለጠ ፡ ታየ ፡ ገበናዬ ፡ ከእሪያዎች ፡ ጋር ፡ ሆነ ፡ መዋያዬ ዘበኝነት ፡ አጣሁ ፡ ጠፋኝ ፡ መላ ፡ ቅጡ ለካስ ፡ ማእረግ ፡ የለም ፡ ከአባት ፡ ቤት ፡ ከወጡ አዝ፦ ወደ ፡ አባቴ ፡ ወደ ፡ ቀድሞ ፡ ቤቴ ፡ እመለሳለሁ እንደ ፡ ልጁም ፡ ባይሆን ፡ እንደ ፡ ባሪያው ፡ እኖራለሁ (፪x) እኔን ፡ ያየኝ ፡ ይቀጣ ፡ ይማር ፡ ከሕይወቴ እርቃናዬን ፡ ቀረሁ ፡ በአባካኝነቴ ሳለሁ ፡ ባባቴ ፡ ቤት ፡ ወዜን ፡ ያየ ፡ ማነው? ያስብ ፡ ጠንቀቅ ፡ ይበል ይህ ፡ ዓለም ፡ ክፉ ፡ ነው ፡ አጫርሶ ፡ ዝም ፡ ይላል ምንም ፡ ይሁን ፡ ምንም ፡ የአባት ፡ ቤት ፡ ይሻላል አዝ፦ ወደ ፡ አባቴ ፡ ወደ ፡ ቀድሞ ፡ ቤቴ ፡ እመለሳለሁ እንደ ፡ ልጁም ፡ ባይሆን ፡ እንደ ፡ ባሪያው ፡ እኖራለሁ (፪x) አዋጅን ፡ የምትሰማ ፡ ያለህ ፡ የትም ፡ ቦታ ጨለማ ፡ የዋጠህ ፡ የጠፋህ ፡ ከጌታ እንጀራውን ፡ በልተህ ፡ ፈውሱን ፡ ተቀብለህ ድርሻህን ፡ በመውሰድ ፡ የሄድከው ፡ ኮብልለህ እስኪ ፡ መለስ ፡ በል ፡ ወደ ፡ ጥንቱ ፡ ቤትህ አይጨክንብህም ፡ ርህሩህ ፡ ነው ፡ አባትህ ለጣትህ ፡ ቀለበት ፡ ለእግርህ ፡ ጫማ ያጐናፅፍሃል ፡ በመንፈሱ ፡ ሸማ ፍሪዳ ፡ ይታረድ ፡ ወገን ፡ ደስ ፡ ይበለው ለነገ ፡ አታሳድር ፡ መዳንህ ፡ ዛሬ ፡ ነው አዝ፦ ወደ ፡ አባቴ ፡ ወደ ፡ ቀድሞ ፡ ቤቴ ፡ እመለሳለሁ እንደ ፡ ልጁም ፡ ባይሆን ፡ እንደ ፡ ባሪያው ፡ እኖራለሁ (፪x)