Loading
Singer
ያልተቀበልነው - ምን ምን አለ? ሁሉ በርሱ ነው - ሞላ፥ ጎደለ ለገባው ቃሉ - የታመነ እግዚአብሔር ነው - የገነነ እግዚአብሔር ብቻ ነው - የመስጠት ልኩ ተቀብላችሁ - ክብሩን አትንኩ ቢጎል ቢሞላ - ለነፍስ ዋስትና ሲጠማን ምንጭ ነው - ሲርበን መና! - [አዝ] ደከመኝ አይል - አጋዥ አይሻ በራሱ ሙሉ - የራሱ ጋሻ ታክቶት አላየን - እንደዛለ ሰው አንዴም አልሰማን - ጉልበቱ ሲያንሰው! [አዝ] ይኼ ማን ነው - ባህር ያቆመ የህዝቡን ማዳን - የፈፀመ? ኧረ ይህ ማን ነው - የማዕዘን አለት ፍጥረታት ሁሉ - የሚገዙለት? በ'ፍኙ የሚሰፍር - ያሉትን ቀላያት በምድርም ያሉ - የሰማይም ሰማያት፤ በኃይል የታሰሩትን - ፈቶ የለቀቀ የሚጋፉን ዓለማት - ሰብስቦ ያረቀ! ----------- ጫንቃችን ላይ በዝቶ - የኃጢያት እዳችን በፍርድ ስር ሳለን - መውጫ መንገዳችን፤ የብርሃን መገኛ - የሰው ልብ ያበራ የፍጥረት ፈጣሪ - ማዳኑን የሰራ! በ'ፍኙ የሚሰፍር - ያሉትን ቀላያት በምድርም ያሉ - የሰማይም ሰማያት፤ የብርሃን መገኛ - የሰው ልብ ያበራ የፍጥረት ፈጣሪ - ማዳኑን የሰራ! ኢየሱስ ክርስቶስ - መድኅኒተ አለሙ በፍጥረት ሁሉ ፊት - ገናና ነው ስሙ። 2x