Loading
Singer
በሄድኩበት ፡ ሁሉ ፡ ሞገስ ፡ እየሆንከኝ ያንን ፡ ክፉ ፡ ዘመን ፡ በድል ፡ አሻገርከኝ አሃሃሃሃ ፡ በድል ፡ አሻገርከኝ እጄን ፡ በጅህ ፡ ይዘህ ፡ እያበረታኸኝ ያንን ፡ ድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ በድንቅ ፡ አሳለፍከኝ አሃሃሃሃ ፡ በድንቅ ፡ አሳለፍከኝ አዝ፦ ወዳጄ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔስ ፡ ያደረከው እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x) ወዳጄ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔስ ፡ ያደረከው እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x) አያልቅም ፡ ውለታህ ፡ ባወራው ፡ ብተርከው (፬x) ለውለታህ ፡ ምላሽ ፡ ከሆነ ፡ መሥጋና (፪x) ለስጦታህ ፡ ምላሽ ፡ ከሆነ ፡ ምሥጋና (፪x) ልዘምር ፡ እንደገና ፤ ላምልክህ ፡ እንደገና (፬x) አባት ፡ ሆነህ ፡ አሳድገኸኛል ከእናት ፡ በላይ ፡ ራርተህልኛል የቅርቤ ፡ ነህ ፡ ውዴ ፡ ለእኔ መሳይ ፡ አጣሁልህ ፡ በዘመኔ (፪x) አዝ፦ ወዳጄ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔስ ፡ ያደረከው እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x) ወዳጄ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔስ ፡ ያደረከው እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x) አያልቅም ፡ ውለታህ ፡ ባወራው ፡ ብተርከው (፬x) ወግ ፡ ማዕረጌ ፡ ክብሬ ፡ ልበልህ ውዴ ፡ ብዬ ፡ ስላልጠገብሁህ የልቤን ፡ የውስጤን ፡ ባይገልጸውም እንዲያው ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ ልበለዉ የፍቅርህን ፡ ልኩን ፡ ባልገልጸዉ እንዲያው ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ ልበለዉ