Loading
Singer
የማይከዳ ፡ ትቶ ፡ የማይሄድ ሃብት ፡ ንብረት ፡ ፊት ፡ አይቶ ፡ የማይወድ እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ ማን ፡ አለ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለ (፪x) ታናሽነቴን ፡ ያልናቀ ፡ እጁን ፡ ዘርግቶ ፡ ጠራኝ እወድሃለሁኝ ፡ ልጄ ፡ አንተ ፡ የእኔ ፡ ነህ ፡ አለኝ በስደት ፡ በባርነት ፡ አገር ፡ ታሪኬን ፡ በክብር ፡ ቀየረ ብቻዬን ፡ ነኝ ፡ ባልኩበት ፡ ጊዜ ፡ ለካ ፡ ጌታ ፡ አብሮኝ ፡ ነበረ (፪x) (አይቻለሁ) ፡ ወዳጅ ፡ መስሎ ፡ ስንቱ ፡ ቀርቦኝ (አይቻለሁ) ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ሲሄድ ፡ ጥሎኝ (አይቻለሁ) ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ስቲዘኝ (አይቻለሁ) ፡ በድካሜ ፡ እንኳን ፡ ተሸከምከኝ አይለወጥ ፡ ፍቅርህ አይሰለች ፡ ትክሻህ የሚያልፈው ፡ ሁሉ ፡ ሲጸየፈኝ ቁስሌን ፡ ጠራርገህ ፡ አነሳኸኝ አይለወጥ ፡ ፍቅርህ አይሰለች ፡ ትክሻህ የሚያልፈው ፡ ሁሉ ፡ ሲጸየፈኝ አባት ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የተጠጋኸኝ (አይለወጥ ፡ ፍቅርህ (፫x)) (አይሰለች ፡ ትክሻህ) ከወንድም ፡ አብልጦ ፡ የሚጠጋጋ ፡ ወዳጄ እኔስ ፡ አላየሁም ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ የሚመች ሁሉም ፡ በሸሸበት ፡ በዚያ ፡ በከባዱ ፡ ጊዜ ኢየሱስ ፡ አይደለም ፡ ዎይ ፡ ያወጣኝ ፡ ከሃዘን ፡ ከትካዜ (፪x) አቤት ፡ የአንተስ ፡ ፍቅር ፡ አቤት ፡ ቸርነትህ ለጠላትስ ፡ አይቀር ፡ በመስቀል ፡ መሞትህ ልቤ ፡ አቅም ፡ አጣ ፡ በፍቅርህ ፡ ጉልበት ተሸነፍኩኝ ፡ በቃ ፡ ገዛኝ ፡ ማንነትህ (፪x) ማን ፡ ብዬ ፡ እጠራሃለሁ ፍቅርህ ፡ ከምለው ፡ በላይ ፡ ነው ኢየሱሴ ፡ ትለያለህ እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ ማን ፡ ወዳጅ ፡ አለ (፪x)