Loading
Singer
አዝ፦ ውበት ፡ እና ፡ ግርማህ ፡ ያማረ ሞገስህ ፡ እጅግ ፡ የከበረ ዝናህን ፡ ሰምቼ ፡ መጣሁ ከሰማሁት ፡ በላይ ፡ ሆኖ ፡ አየሁ አስገረመኝ ፡ አገዛዝህ ሁሉን ፡ በፍቅር ፡ ይዘህ አያልቅም ፡ ቢነገር ፡ ስራህ ጌታዬ ፡ እጅግ ፡ ልዩ ፡ ነህ ልዩ ፡ ነህ (፫x) ጌታዬ ፡ እጅግ ፡ ልዩ ፡ ነህ (፪x) ከአማልክት ፡ መካከል ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው በላይ ፡ በሰማይ ፡ በታች ፡ በምድር አንተን ፡ የሚመስል ፡ አጣሁ ኃያልና ፡ የተፈራህ ሥልጣናት ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ነው መንግሥትህ ፡ ዘለዓለም እጅግ ፡ የጸና ፡ ነው ዝናህን ፡ አውርቼ ፡ አልጨርሰው አይበቁኝምና ፡ ቃላት ለመግለጽ ፡ የአንተን ፡ ማንነት ስለዚህ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ ላምልክ ሕይወቴን ፡ ለአንተ ፡ ላስገዛልህ (፪x) አዝ፦ ውበት ፡ እና ፡ ግርማህ ፡ ያማረ ሞገስህ ፡ እጅግ ፡ የከበረ ዝናህን ፡ ሰምቼ ፡ መጣሁ ከሰማሁት ፡ በላይ ፡ ሆኖ ፡ አየሁ አስገረመኝ ፡ አገዛዝህ ሁሉን ፡ በፍቅር ፡ ይዘህ አያልቅም ፡ ቢነገር ፡ ስራህ ጌታዬ ፡ እጅግ ፡ ልዩ ፡ ነህ ልዩ ፡ ነህ (፫x) ጌታዬ ፡ እጅግ ፡ ልዩ ፡ ነህ (፪x) ብዙ ፡ ኃያላን ፡ የነበሩ ታላዝ ፡ ነን ፡ ብለው ፡ የተነሱ ዛሬ ፡ ቢፈለጉ ፡ አንዳቸውም ፡ የሉ ሞት ፡ አሸንፏቸው ፡ ተረሱ አንተ ፡ ግን ፡ ያለህ ፡ የነበርህ ለዘለዓለም ፡ ትኖራለህ አልፋና ፡ ኦሜጋ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ የሚስተካከልህ ፡ የሌለህ ስለ ፡ አንተ ፡ ዘምሬ ፡ መቼ/መች ፡ ጠገብኩ (፪x) ሥምህን ፡ ጠርቼ ፡ አልረካሁ (፪x) ያንስብሃል ፡ ኢሄ ፡ አይበቃህ (፪x) ከዚም ፡ በላይ ፡ ክብር ፡ ይብዛልህ (፪x) አይበቃህምና ፡ ልጨምር ፡ ገና ከልቤ ፡ ይፍለቅ ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና (፬x)