Loading
Singer
ዛሬ ፡ ታይቶ ፡ ነገ ፡ ሊጠፋ ድንገት ፡ ሊሰበር ፡ እንደሸክላ ላጭሩ ፡ ዘመኔ ፡ ቀጠልኩለት ፡ ዕድሜ መላ ፡ ዘይጃለሁ ፡ እፎይ ፡ ትበል ፡ ነፍሴ አዝ፦ ለሕይወቴ ፡ ዋጋ ፡ ሰጠሁ ፡ ኢየሱስን ፡ ማግኘቴ ከሞት ፡ ወዲያ ፡ እሻገር ፡ ዘንድ ፡ ላልሞት ፡ ሕያው ፡ ሆኜ ሰረገላው ፡ አሳፈረኝ ፡ ሊያሻግረኝ ፡ ማዶ ጠርቶኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ወደ ፡ እረፍቱ ፡ እንዳልጠፋ ፡ ወዶ (፪x) ሞት ፡ እንደው ፡ አይቀርም ፡ ሰው ፡ ግን ፡ ሞት ፡ ይፈራል ከበሩ ፡ ላይ ፡ ደርሶ ፡ ሊወስደው ፡ ሲመጣ ፡ በእምባ ፡ ዐይኑ ፡ አይቶታል ነፍሱን ፡ ይወስዳታል ፡ ድምጹን ፡ ሳያሰማ ላይመልሰው ፡ ዳግም ፡ አንዴም ፡ ሳያቅማማ ነፍሱን ፡ ይወስዳታል ፡ ኮቴ ፡ ሳያሰማ ላይመልሰው ፡ ዳግም ፡ አንዴም ፡ ሳያቅማማ በድኑን ፡ ታቅፈው ፡ ወዳጅ ፡ ዘመዶቹ ቢያለቅሱ ፡ አይመለስ ፡ ደረት ፡ እየደቁ በእርግጥ ፡ በኢየሱስ ፡ አምኖ ፡ ካልዳነ ፡ ሰው ዋይ ፡ ዋይ ፡ ይበሉለት ፡ ደግመው ፡ ያልቅሱለት ግን ፡ በክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ አምኖ ፡ ከዳነ ፡ ሰው እልል ፡ ይበሉለት ፡ ለቅሷቸውን ፡ ትተው አዝ፦ ለሕይወቴ ፡ ዋጋ ፡ ሰጠሁ ፡ ኢየሱስን ፡ ማግኘቴ ከሞት ፡ ወዲያ ፡ እሻገር ፡ ዘንድ ፡ ላልሞት ፡ ሕያው ፡ ሆኜ ሰረገላው ፡ አሳፈረኝ ፡ ሊያሻግረኝ ፡ ማዶ ጠርቶኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ወደ ፡ እረፍቱ ፡ እንዳልጠፋ ፡ ወዶ (፪x) ከንቱ ፡ ለሆነ ፡ ነገር ፡ ታይቶ ፡ ለሚጠፋ ለሕይወት ፡ ዋስትና ፡ አጥተህ ፡ ወንድሜ ፡ አትልፋ ክርስቶስን ፡ አምነህ ፡ ዋጋ ፡ ስጥ ፡ ለሕይወትህ ታይቶ ፡ የሚጠፋ ፡ እንዳያታልልህ ነይ ፡ እህቴ ፡ ና ፡ ወንድሜ ዘመኑ ፡ አልቋል ፡ ዛሬ ፡ ነገ ፡ አትበል የመዳን ፡ ቀን ፡ ዛሬ ፡ ነው ፡ እንዳትወላውል ከጨለማ ፡ ከሞት ፡ ከሞት ፡ አምልጥ ፡ እሩጥ ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ለሕይወትህ ፡ ዋጋ ፡ ስጥ የመዳንህ ፡ ቀን ፡ ዛሬ ፡ ነው ፡ እባክህ ፡ ወገኔ አትወላውል ፡ አትባክን ፡ ትረፍ ፡ ከኩነኔ (፪x) ትረፍ ፡ ከኩነኔ (፪x)