Loading
Singer
የምሬት ፡ ጊዜ ፡ የአምባ ፡ ጊዜሽ ያንን ፡ መከራ ፡ ጉስቁልናሽ ተመልክቶታል ፡ በቃ ፡ አታልቅሺ ዘምሪ ፡ ዕልል ፡ በይ ፡ ጽዮን ፡ ተነሺ (፪x) ጽዮን ፡ ሆይ ፡ ተነሺ አዝ፦ ጽዮን ፡ ሆይ ፡ ተነሺ ፡ ዉለታውን ፡ አትርሺ ይበቃል ፡ የለቅሶ ፡ ዘመን ፡ እምባሽን ፡ አብሺ ያንን ፡ ክፉ ፡ ዘመን ፡ በማን ፡ ተሻገርሽ አሁንም ፡ ሊረዳሽ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ጌታሽ የእግዚአብሄር ፡ ጆሮዎች ፡ ጸሎትሽን ፡ ሰምተዋል አንቺን ፡ ለማዳን ፡ እጁን ፡ ዘርግቷል ያንን ፡ መከራ ፡ የሚያስረሳሽ ይዞልሽ ፡ መጥቷል ፡ ድንቅ ፡ በረከቱን (፪x) አዝ፦ ጽዮን ፡ ሆይ ፡ ተነሺ ፡ ዉለታውን ፡ አትርሺ ይበቃል ፡ የለቅሶ ፡ ዘመን ፡ እምባሽን ፡ አብሺ ያንን ፡ ክፉ ፡ ዘመን ፡ በማን ፡ ተሻገርሽ አሁንም ፡ ሊረዳሽ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ጌታሽ ትላንት ፡ በለቅሶ ፡ ለዘራሺው ፡ ዘርሽ መጥቶልሻል ፡ ጌታ ፡ በሳቅ ፡ ሊያሳጭድሽ ያኔ ፡ በመከራሽ ፡ የገባልሽን ፡ ቃል ጌታ ፡ ሊፈጽመው ፡ ከማደሪያው ፡ ነቅቷል (፪x) አዝ፦ ጽዮን ፡ ሆይ ፡ ተነሺ ፡ ዉለታውን ፡ አትርሺ ይበቃል ፡ የለቅሶ ፡ ዘመን ፡ እምባሽን ፡ አብሺ ያንን ፡ ክፉ ፡ ዘመን ፡ በማን ፡ ተሻገርሽ አሁንም ፡ ሊረዳሽ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ጌታሽ