Loading
Singer
የሰማያት ፡ ዳርቻ ፡ ሰሪ የምድርም ፡ ሁሉ ፡ ፈጣሪ አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ እግዚአብሔር ፡ ኤልሻዳይ ኧረ ፡ አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ እግዚአብሔር ፡ ሁሉን ፡ ቻይ አላቋርጥ ፡ ማንኳኳቴን ፡ እስኪከፈትልኝ ፡ ደጁ ፀሎቴንም ፡ እስኪሰማ ፡ እስኪዘረጋላኝ ፡ እጁ ዘንበል ፡ እስኪል ፡ ከዙፋኑ ፡ እስኪበዛልኝ ፡ ምሕረቱ ዝም ፡ አልልም ፡ አላቆምም ፡ መፈለጌን ፡ ማየት ፡ ፊቱን እግዚአብሔር ፡ በዙፋኑ ፡ ያለው ፀሎቴን ፡ ይሰማል ፡ አውቃልሁ አምላኬ ፡ በማደሪያው ፡ ያለው ይራራል ፡ ይምራል ፡ አምናለሁ (፪x) እስኪለወጥ ፡ በምስጋና ፡ የለቅሶ ፡ የእንባ ፡ ጩኸቴ ሙሉ ፡ ሆኖ ፡ እንኪመጣ ፡ እስኪለቀቅ ፡ በረከቴ ከአንደበቱ ፡ እስኪወጣ ፡ የበረከት ፡ ንግግር አልነሳም ፡ ዞር ፡ አልልም ፡ ከዙፋኑ ፡ ከእግሩ ፡ ስር እግዚአብሔር ፡ በዙፋኑ ፡ ያለው ፀሎቴን ፡ ይሰማል ፡ አውቃልሁ አምላኬ ፡ በማደሪያው ፡ ያለው ይራራል ፡ ይምራል ፡ አምናለሁ (፪x) የተስፋውን ፡ ቃል ፡ አስቦ ፡ ሊፈጽመው ፡ እስኪነሣ የምድሬኔም ፡ ኃጢአት ፡ በደል ፡ ይቅር ፡ ብሎ ፡ እስኪረሳ ክብሩን ፡ ዳግም ፡ እስኪመልስ ፡ በቅዱሱ ፡ ማደሪያው አላቆምም ፡ ክርክሬን ፡ እስኪነሣ ፡ ከስፍራው የሚሰማ ፡ የሚመልስ ፡ የሚምር ፡ ነው ፡ የሚራራ (፪x) በጎነቱ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ በሞገሱ ፡ የተፈራ (፪x) ቸር ፡ እንደእርሱ ፡ ስለሌለ ፡ በምድር ፡ ቢሆን ፡ በሰማይ (፪x) አንዲቷም ቀን አታልፍብኝ ፡ ያምላኬን ፡ ፊቱን፡ ሳላይ (፬x)