Loading
ቢያሳዝንም ፡ እንደምሕረቱ ፡ ብዛት ፡ ይራራልና የሰውን ፡ ልጆች ፡ ከልቡ ፡ አያስጨንቅምና አፌን ፡ በአፈር ፡ ውስጥ 2x አኖራለው ዝም ፡ ብዬ ፡ ማዳኑን ፡ ተስፋ ፡ አደርጋለው እግዛብሄር ፡ የታመነ ፡ ነው 3x ጌታዬ ፡ ለዘላለም ፡ አይጥልም ጸሎቴን ፡ ቢከለክልም ፡ ጩህቴን ፡ ባይሰማ ልመናን ፡ ሳበዛ ፡ ፊቱን ፡ ከእኔ ፡ ቢሰውርም መንገዴን ፡ እስቲ ፡ ልመርምር ወደ ፡ እግዛብሄር ፡ ልመለስ ልቤን ፡ ከእጄ ፡ ጋር ፡ በሰማይ ፡ ወደለው ፡ ላንሳ በሃጥያቴ ፡ ቢቆጣም ፡ እንኳ ፡ ስለዓመጻዬም ፡ ቢቀጣኝም እግዛብሄር ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ፍጽሞ ፡ አይተወኝም ከሰማይ ፡ እስኪጐበኘኝ ፡ እስኪመለከተኝ ፡ ድረስ ዓይኔ ፡ ሳታቋርጥ ፡ እምባዬን ፡ ታፍስስ ፡ ታፍስስ በጥቂት ፡ ቁጣ ፡ ፊቱን ፡ ከእኔ ፡ ቢሰውርም በዘላለም ፡ ቸርነት ፡ ይምራል ፡ እግዚአብሔር
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.