Loading
Singer
አዝ፦ ፀጋህ ፡ ያግዘኝ ፡ እንጂ መንፈስህ ፡ ይምራኝ ፡ እንጂ ምን ፡ አቅም ፡ አለኝ ፡ እኔ በአንተው ፡ ነው ፡ ሰው ፡ መሆኔ (፪x) ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ጌታዬ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ዋስትናዬ (፪x) የዘለዓለም ፡ እቅድህን ፡ በእኔ ፡ ያለህን ፡ አላማ ፡ ፈጽሜ ፡ ደስ ፡ እንዳሰኝህ ፡ እርዳኝ ፡ ከሐሳብህ ፡ ልስማማ ። በሚሰማ ፡ በሚታየው ፡ እንዳልወሰድ ፡ ከቤትህ ምራኝ ፡ እጆቼን ፡ ያዝና ፡ ሁልጊዜ ፡ ልኑር ፡ በፊትህ (፪x) እርዳኝ ፡ እንዳላሳዝንህ ፡ እርዳኝ (፫x) እርዳኝ ፡ በቤትህ ፡ እንድኖር ፡ እርዳኝ አዝ፦ ፀጋህ ፡ ያግዘኝ ፡ እንጂ መንፈስህ ፡ ይምራኝ ፡ እንጂ ምን ፡ አቅም ፡ አለኝ ፡ እኔ በአንተ ፡ ነው ፡ ሰው ፡ መሆኔ (፪x) ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ጌታዬ (ጌታዬ) አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ዋስትናዬ (ዋስትናዬ) (፪x) እምነት ፡ እንደጐደለው ፡ ሰው ፡ መጠራቴ ፡ እንዳይቀርብኝ ፡ የፈቃድህን ፡ ምሥጢር ፡ እንዳውቅ ፡ ጥበብ ፡ ማስተዋልን ፡ ስጠኝ ስንፍናዬ ፡ ከኔ ፡ ርቆ ፡ እንዲያምር ፡ መጨረሻዬ መልካም ፡ ፍሬ ፡ እንዲገኝብኝ ፡ ደግፈኝ ፡ ከመነሻዬ ፡ (፪x) እርዳኝ (እርዳኝ) ፡ እንዳላሳዝንህ ፡ እርዳኝ (፫x) እርዳኝ (እርዳኝ) ፡ በቤትህ ፡ እንድኖር ፡ እርዳኝ አዝ፦ ፀጋህ ፡ ያግዘኝ ፡ እንጂ መንፈስህ ፡ ይምራኝ ፡ እንጂ ምን ፡ አቅም ፡ አለኝ ፡ እኔ በአንተ ፡ ነው ፡ ሰው ፡ መሆኔ (፪x) ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ጌታዬ (ጌታዬ) አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ዋስትናዬ (ዋስትናዬ) (፪x)