Loading
Singer
አዝ፦ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ ፀጋ ፡ እፈልጋለሁ ያለ ፡ አንተማ ፡ እርዳታ ፡ እንዴት ፡ እኖራለሁ (፪x) ጉልበቴ ፡ ሳይላላ ፡ ሳይቀንስ ፡ ትጋቴ በቤትህ ፡ መኖር ፡ ነው ፡ ሌት ፡ ተቀን ፡ መሻቴ ልገስግስ ፡ ወደፊት ፡ እየታደሰ ፡ ኃይሌ በመክሊቴ ፡ ላትርፍ ፡ ይብዛ ፡ ማገልገሌ አዝ፦ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ ፀጋ ፡ እፈልጋለሁ ያለ ፡ አንተማ ፡ እርዳታ ፡ እንዴት ፡ እኖራለሁ (፪x) የድል ፡ አድራጊ ፡ ልጅ ፡ ባለ ፡ ድል ፡ አርገኸኝ ሽንፈታም ፡ ነኝ ፡ እያልኩ ፡ ሳወራ ፡ እንዳልገኝ የሰራህልኝን ፡ መልካሙን ፡ ሥራህን እንዳልረሳው ፡ እርዳኝ ፡ ያንን ፡ ውለታህን አዝ፦ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ ፀጋ ፡ እፈልጋለሁ ያለ ፡ አንተማ ፡ እርዳታ ፡ እንዴት ፡ እኖራለሁ (፪x) ፍጻሜዬን ፡ አሳምር ፡ እንደ ፡ ጅማሬዬ በመልካም ፡ ይደምደም ፡ በፊትህ ፡ ሩጫዬ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ከአንተ ፡ ለአንተ ፡ ነውና ይኸው ፡ ክበርብኝ ፡ ዝቅ ፡ ልበልና አዝ፦ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ ፀጋ ፡ እፈልጋለሁ ያለ ፡ አንተማ ፡ እርዳታ ፡ እንዴት ፡ እኖራለሁ (፪x) ለባዕድ ፡ አልሰጥም ፡ ይህን ፡ ጉብዝናዬን ወስኛለሁ ፡ አጽናው ፡ ቅዱሱን ፡ ምርጫዬን ልኑር ፡ እንደ ፡ ቃልህ ፡ ግራ ፡ ቀኙን ፡ ሳላይ እስካገኝ ፡ ርስቴን ፡ እስክገባ ፡ ሰማይ አዝ፦ አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ ፀጋ ፡ እፈልጋለሁ ያለ ፡ አንተማ ፡ እርዳታ ፡ እንዴት ፡ እኖራለሁ (፪x)