Loading
Singer
ሄኖክ ፡ ሞትን ፡ እንዳያይ ፡ በእምነት ፡ ተወሰደ ኖህ ፡ በምድረ ፡ በዳው ፡ መርከብን ፡ አበጀ አብረሃም ፡ እርስቱን ፡ ከነዓንን ፡ ወረሰ ሳራም ፡ በእምነቷ ፡ ኃይሏ ፡ ተመለሰ አዝ፦ ጻድቅ ፡ ግን ፡ በእምነት ፡ በሕይወት ፡ ይኖራል የሚታየውን ፡ ሳይሆን ፡ የማይታየውን ፡ ይረዳል የተስፋውን ፡ ቃል ፡ የሰጠው ፡ የታመነ ፡ ነውና ደካሞች ፡ በእምነት ፡ ጉልበታችሁ ፡ ይጽና (፪x) ነፍሱ ፡ ፍፁም ፡ ደክማ ፡ ትንፋሽ ፡ ተሰውሮ የሚታይ ፡ መመኪያ ፡ ከአፈር ፡ ተቀብሮ ሥጋ ፡ ደግሞ ፡ ዝሎ ፡ ሞት ፡ ሽታ ፡ ሲሸተው ጻድቅ ፡ ግን ፡ በእምነት ፡ ከክርስቶስ ፡ ጋር ፡ ነው አዝ፦ ጻድቅ ፡ ግን ፡ በእምነት ፡ በሕይወት ፡ ይኖራል የሚታየውን ፡ ሳይሆን ፡ የማይታየውን ፡ ይረዳል የተስፋውን ፡ ቃል ፡ የሰጠው ፡ የታመነ ፡ ነውና ደካሞች ፡ በእምነት ፡ ጉልበታችሁ ፡ ይጽና (፪x) ባሕሩን ፡ በበትር ፡ አሻግሮ ፡ የከፈለ ውሃን ፡ እንደ ፡ ግድግዳ ፡ ገትሮ ፡ ያቆመ ዝናብን ፡ ኤልያስ ፡ በእምነት ፡ ከለከለ እስራኤል ፡ በአምላኩ ፡ ጉልበቱ ፡ አየለ አዝ፦ ጻድቅ ፡ ግን ፡ በእምነት ፡ በሕይወት ፡ ይኖራል የሚታየውን ፡ ሳይሆን ፡ የማይታየውን ፡ ይረዳል የተስፋውን ፡ ቃል ፡ የሰጠው ፡ የታመነ ፡ ነውና ደካሞች ፡ በእምነት ፡ ጉልበታችሁ ፡ ይጽና (፪x)