Loading
Singer
ሕግህን ፡ እጽፈዋለሁ ፡ በልቦናዬ እንዲሆን ፡ የሞገስ ፡ ዘውዴ ፡ የአንገት ፡ ድርዬ ሁሌ ፡ ቃልህ ፡ ነውና ፡ የእግሬ ፡ መብራት መንገዴን ፡ የሚያቀናልኝ ፡ በአንተው ፡ ስርዓት (፪x) አቤቱ ፡ እንዳልበድልህ ፡ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን መንገድም ፡ እንዲነጻልኝ ፡ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን በትዕዛዝህ ፡ መንገድ ፡ እንድሮጥ ተንሸራትቼም ፡ እንዳልገባ ፡ ማጥ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን ስንፍናን ፡ ተግቼ ፡ ኃጢአትን ፡ ሳላምጥ ሕይወቴ ፡ በድንገት ፡ እንዳያመልጥ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን ስህተትን ፡ እንዳስተውላት ፡ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን እንድሰወር ፡ ከስውር ፡ ኃጢአት ፡ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን ከጓደኞቼ ፡ ጋር ፡ በሳቅ ፡ ጨዋታ መስመር ፡ እንዳላልፍ ፡ እንዳልረሳ ፡ ጌታ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን የድፍረት ፡ ኃጢአት ፡ ጠፍሮ ፡ እንዳይዘኝ የቃልህ ፡ ፍርሃት ፡ ሁልጊዜ ፡ እንዲያዘኝ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን ቃልህ ፡ ይሁን ፡ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን (፪x) መፅናናት ፡ ሲያስፈልገኝ ፡ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን መከራው ፡ ሲያሳድደኝ ፡ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን ከጠላቴ ፡ ዛቻ ፡ ከምክሩ ፡ እንዳልፈራ ልቤ ፡ እንዲጠበቅ ፡ በምክርህ ፡ እንድመራ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን የኃጥአን ፡ ገመዶች ፡ ሲተበተቡብኝ አለቆች ፡ ተቀምጠው ፡ ሲያሙኝ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን በአመፀኞች ፡ እንዳልቀና ፡ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን የግፍ ፡ እንጀራ ፡ እንዳልበላ ፡ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን የጓዳዬን ፡ ኑሮዬን ፡ ቤቴን ፡ ለመሙላት በከንፈሬ ፡ እንዳልወሰልት ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን እግሬ ፡ እንዲከለከል ፡ ከክፋት ፡ ጐዳና በፈተና ፡ ሁሉ ፡ እምነቴ ፡ እንዲፀና ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን ቃልህ ፡ ይሁን ፡ ትዝታዬ ፡ ቃልህ ፡ ይሁን (፪x) ሕግህን ፡ እጽፈዋለሁ ፡ በልቦናዬ እንዲሆን ፡ የሞገስ ፡ ዘውዴ ፡ የአንገት ፡ ድርዬ ሁሌ ፡ ቃልህ ፡ ነውና ፡ የእግሬ ፡ መብራት መንገዴን ፡ የሚያቀናልኝ ፡ በአንተው ፡ ስርዓት (፪x)