Loading
Singer
ትውስ ፡ ሲለኝ ፡ የጌታዬን ፡ ፍቅር ያደረገልኝ ፡ በጐልጐታ ከአገር ፡ ወደ ፡ አገር ፡ በመንከራተት ፀሐይና ፡ ውርጭ ፡ ሲፋረቁበት ይሁዳ ፡ ሸጦት ፡ ጴጥሮስ ፡ ሲክደው ተከታዮቹም ፡ ጥለውት ፡ ሲሸሹ የፊጥኝ ፡ ታስሮ ፡ ለፍርድ ፡ ሲነዳ ጥፊ ፡ እና ፡ ግርፉ ፡ ሲወርድበት አዝ፦ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ያ ፡ መድህኔ በእንጨት ፡ ላይ ፡ የሞተው ፡ ስለእኔ ትውስ ፡ ይለኛል ፡ የመስቀል ፡ ፍቅሩ ያደረገልኝ ፡ ውለታው ፡ ሁሉ አልራሩለትም ፡ አስረው ፡ ሲገርፉት ያን ፡ መልከመልካም ፡ እሩፍሩሁን ፡ ፈጠሪ የማይችለውን ፡ መስቀል ፡ አሲዘው መድህናቸውን ፡ ለፍርድ ፡ ሲወስዱ ሲጮህ ፡ ሲያነባ ፡ በጣር ፡ ተከቦ በደም ፡ ላብ ፡ ባሕር ፡ ሆኖ ፡ ሲያነባ ፡ ሲያነባ ሲወድቅ ፡ ሲነሳ ፡ አባ ፡ አባ ፡ ሲል ተሰቃየልኝ ፡ ነፍሱ ፡ እስክትዘልቅ አዝ፦ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ያ ፡ መድህኔ በእንጨት ፡ ላይ ፡ የሞተው ፡ ስለእኔ ትውስ ፡ ይለኛል ፡ የመስቀል ፡ ፍቅሩ ያደረገልኝ ፡ ውለታው ፡ ሁሉ ይረሳኛል ፡ ወይ ፡ ያ ፡ የጣር ፡ ጊዜው መድሃኒቴን ፡ እየተሳለቁበት ከመስቀል ፡ ውረድ ፡ ራሽን ፡ አድን እያሉ ፡ ጠላቶች ፡ ሲያሾፉበት ጨለማ ፡ ውጦን ፡ የነበርነውን እኛን ፡ ለማዳን ፡ ከክብሩ ፡ ወርዶ የዓለምን ፡ ኀጢአት ፡ ያስወገደውን ታላቁን ፡ መድህን ፡ ነፍሴ ፡ አትረሳውም አዝ፦ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ያ ፡ መድህኔ በእንጨት ፡ ላይ ፡ የሞተው ፡ ስለእኔ ትውስ ፡ ይለኛል ፡ የመስቀል ፡ ፍቅሩ ያደረገልኝ ፡ ውለታው ፡ ሁሉ (፪x)