Loading
Singer
ትላንትን ፡ ሳስበው ፡ በዛሬ ፡ ላይ ፡ ሆኜ ስንቱን ፡ አልፊያለሁ ፡ እኔ ፡ አንተን ፡ መክሬ (፪x) ምንድን ፡ ነው ፡ ስል ፡ እንደዚህ ፡ ያቆመኝ ምህረትህ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ትዝ ፡ የሚለኝ አባት ፡ መሆንህ ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ትዝ ፡ የሚለኝ አዝ፦ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ያነባ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ የጣለ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ አንተ ፡ ሞትህ ፡ ለእኔ ፡ እኔን ፡ ልታኖር ትዝ ፡ ይለኛል ፡ መነሻ ፡ ሳይኖረኝ ፡ እንዲህ ፡ የወደድከኝ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ በፍቅርህ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ኧረ ፡ እኔን ፡ ያስጣለኝ (፪x) ለካስ ፡ ልክ ፡ ነበር ፡ ስትነግረኝም ፡ ያኔ ዛሬ ፡ ደርሼበት ፡ አይቻለሁ ፡ በዓይኔ (፪x) አላማርርህም ፡ ሳስብ ፡ መፈጠሬን ለእኔ ፡ ተስማምቶኛል ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ መኖሬ (፪x) አዝ፦ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ያነባ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ የጣለ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ አንተ ፡ ሞትህ ፡ ለእኔ ፡ እኔን ፡ ልታኖር ትዝ ፡ ይለኛል ፡ መነሻ ፡ ሳይኖረኝ ፡ እንዲህ ፡ የወደድከኝ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ በፍቅርህ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ኧረ ፡ እኔን ፡ ያስጣለኝ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ርህሩሁን ፡ አብርደህ ፡ በረድ ፡ ስታኖረኝ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ እንደ ፡ አባት ፡ ሆነህ ፡ መክረህ ፡ ያሳደከኝ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ያንን ፡ ምድረበዳ ፡ በአንተ ፡ ያለፍኩበት ትዝ ፡ ይለኛል ፡ በሕይወት ፡ ያኖረኝ ፡ የምህረትህ ፡ ብዛት ነፋሱም ፡ ሳይነፍስ ፡ አይኖርም ፡ ደመና በስብከት ፡ ሞኝነት ፡ ተቀበልኩህና (፪x) ስለ ፡ አንተ ፡ ሲወራ ፡ ከሩቁ ፡ ሰምቼ ቀርቤ ፡ አየሁኝ ፡ ማዳንን ፡ በዓይኖቼ አባት ፡ መሆንህን ፡ አየሁኝ ፡ በዓይኖቼ አዝ፦ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ርህሩሁን ፡ አብርደህ ፡ በረድ ፡ ስታኖረኝ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ እንደ ፡ አባት ፡ ሆነህ ፡ መክረህ ፡ ያሳደከኝ ትዝ ፡ ይለኛል ፡ ያንን ፡ ምድረበዳ ፡ በአንተ ፡ ያለፍኩበት ትዝ ፡ ይለኛል ፡ በሕይወት ፡ ያኖረኝ ፡ የምህረትህ ፡ ብዛት (፪x)