Loading
Singer
አንተ ፡ የኔ ፡ የራሴ ፡ የግሌ ፡ የኔ ባስጨናቂው ፡ ለት ፡ ለኔ ፡ ደርሰህ በጨለማ ፡ እኔ ፡ ላይ ፡ ብርሃን ፡ ይብራ ፡ ብለህ ታሪኬን ፡ ለውጠህ ፣ ታዲያ ፡ ልበልህ ፡ እንጂ ፡ አንተ ፡ የኔ (፪x) ማን ፣ ኧረ ፡ ማን ፣ ማን ይወስድብኛል ፡ አንተን ፡ ከኔ (፪x) ማን ፣ ኧረ ፡ ማን ፣ ማን ይወስድብኛል ፡ አንተን ፡ ከኔ (፪x) ተማመለህ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ በጭንቅ ፡ የወለድከኝ ፡ በጎልጎታ እድሜዬን ፡ በሙሉ ፡ ሰጥሃለሁ ዘላለም ፡ ለቃልህ ፡ እገዛለሁ ፣ እገዛለሁ ታዲያ ፣ ልዘምር ፡ እንጂ ልቀኝ ፡ እንጂ ለባለውለታዬ ፡ ልኑር ፡ እንጂ ፡ አሃሃሃ ታዲያ ፡ ታዲያ (፪x) እንደመሸ ፡ አይቀርም ፡ ለሊቱ ፡ ይነጋል (፬x) ማንጋት ፡ ልማድህ ፡ ነውና ፣ ማንሳት ፡ ልማድህ ፡ ነወና ማክበር ፡ ልማድህ ፡ ነወና ፣ ማስዋብ ፡ ልማድህ ፡ ነውና ውዴ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ እኔም ፡ ደግሞ ፡ የእርሱ ፡ ነኝ ፡ የየሱስ ፡ ነኝ (፪x) ማንም ፡ አይገባም ፡ በመሀላችን ጉድለት ፡ የሌለበት ፡ ነው ፡ ፍቅራችን ጊዜም ፡ ሁኔታም ፡ አይሽረዉም ፡ ለኔስ ፡ ኢየሱሴ ፡ ልዩ ፡ ነዉ ፣ ልዩ ፡ ነዉ ታዲያ ፣ ልዘምር ፡ እንጂ ልቀኝ ፡ እንጂ ለባለውለታዬ ፡ ልኑር ፡ እንጂ ፡ አሃሃሃ ታዲያ ፡ ታዲያ (፪x) አንተ ፡ የኔ ፡ የራሴ ፡ የግሌ ፡ የኔ ባስጨናቂው ፡ ለት ፡ ለኔ ፡ ደርሰህ በጨለማ ፡ እኔ ፡ ላይ ፡ ብርሃን ፡ ይብራ ፡ ብለህ ታሪኬን ፡ ለውጠህ ፣ ታዲያ ፡ ልበልህ ፡ እንጂ ፡ አንተ ፡ የኔ (፪x)