Loading
Singer
አዝ፦ ተይ ፡ ነፍሴ የአምላክሽን ፡ ቃል ፡ ስሚና ግራ ፡ ቀኙን ፡ ተይውና ኋላ ፡ ደግሞ ፡ እንዳይቆጭሽ ከአምላክሽ ፡ ጋር ፡ ተጣልተሽ እርሱ ፡ ነው ፡ ሚረባሽን ፡ ሚያውቅልሽ ከእርሱ ፡ ሌላ ፡ አትፈልጊ ፡ የሚረባሽን አሃሃ ፡ አምላክሽ ፡ አለ ፣ አሃሃ ፡ ሚያስብልሽ አሃሃ ፡ ግራና ፡ ቀኙን ፣ አሃሃ ፡ ምን ፡ አሳየሽ አሃሃ ፡ እርሱስ ፡ ስለአንቺ ፣ አሃሃ ፡ ቆስሏልና???? አሃሃ ፡ ሌላ ፡ አትፈልጊ ፣ አሃሃ ፡ አይጠቅምምና ኤሄ ፡ ሞልቶ ፡ ላይሞላ ኤሄ ፡ ለዓለም ፡ ነገር ነፍሴ ፡ አትጨነቂ ፡ የቀረው ፡ ይቅር ኤሄ ፡ ሁሉ ፡ ከንቱ ፡ ነው ኤሄ ፡ የከንቱ ፡ ከንቱ ነፍሴ ፡ ቃሉ ፡ ይሻላል ፡ የእርሱ ፡ የአንደበቱ እኔ ፡ ደግሞ ፡ ወይ ፡ ለራሴ ቀን ፡ አስቦ??? ፡ ለክብር ፡ ነፍሴ የሰጠኀኝ ፡ ፈራሽ ፡ ሥጋዬ ላይሆነኝ ፡ መከበሪያዬ አባትዬ ፡ ባክህ ፡ አደራ በዘመኔ ፡ ስራህን ፡ ልስራ አስከብሬህ ፡ ልኑር ፡ ለክብርህ ስምህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ እንዲጠራ አዝ፦ ተይ ፡ ነፍሴ የአምላክሽን ፡ ቃል ፡ ስሚና ግራ ፡ ቀኙን ፡ ተይውና ኋላ ፡ ደግሞ ፡ እንዳይቆጭሽ ከአምላክሽ ፡ ጋር ፡ ተጣልተሽ እርሱ ፡ ነው ፡ ሚረባሽን ፡ ሚያውቅልሽ ከእርሱ ፡ ሌላ ፡ አትፈልጊ ፡ የሚረባሽን አሃሃ ፡ አታስጨንቂኝ ፣ አሃሃ ፡ አታውኪኝ አሃሃ ፡ ወዲህና ፡ ወዲያ ፣ አሃሃ ፡ አትበይቢኝ አሃሃ ፡ የዓለም ፡ ብልጭልጭ ፣ አሃሃ ፡ መልኩ ፡ ውበቱ አሃሃ ፡ ሁሉም ፡ ጠፊ ፡ ነው ፣ አሃሃ ፡ ደርሷል ፡ ሰዓቱ ኤሄ ፡ ኀጢአት ፡ ብትሰሪ ኤሄ ፡ ትሞቻለሽ ነፍሴ ፡ ጽድቅን ፡ ብትሰሪ በሕይወት ፡ ትኖሪያለሽ ኤሄ ፡ እንዳያዝንብሽ ኤሄ ፡ የሞተልሽን ነፍሴ ፡ ለጽድቅ ፡ ንቂ በሕይወት ፡ ለሚያኖርሽን ሥጋ ፡ ነቅቶ ፡ መንፈስ ፡ ቢደክም መንፈስ ፡ ነቅቶ ፡ ሥጋ ፡ ሲደክም ለበረታው ፡ ላሸነፈው ፡ ብትወግኚ ፡ ለበለጠው ነፍሴ ፡ ዕውቀት ፡ ፍቃድ ፡ አለሽ ተገዢለት ፡ ለታደገሽ ለግዚአብሄር ፡ ለስሙ ፡ ኑሪ በሰማይ ፡ ቤት ፡ ፊቱ ፡ እንዳታፍሪ