Loading
Singer
አዝ:- ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ከመንገድ ፡ አትቅሪ ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ አትቅሪ (፪x) እርስት ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ ፣ መኖሪያ ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ ክብር ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ ፣ አክሊል ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ እባክሽን ፡ ስሚ ፣ ልምከርሽ ፡ በደምብ ፡ አስተውዪ እያቸው ፡ በምድር ፡ የሚሮጡ ፣ ለሚጠፋው ፡ አክሊል ፡ ሲተጉ እርግጥ ፡ ነው ፡ ክርስትና ፡ ያማል ፣ ከኖሩ ፡ ዋጋ ፡ ያስከፍላል ከታገልሽ ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ ያልፋል ፣ ጠብቂ ፡ ኢየሱስ ፡ ይመጣል አዝ:- ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ከመንገድ ፡ አትቅሪ ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ አትቅሪ (፪x) እርስት ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ ፣ መኖሪያ ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ ክብር ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ ፣ አክሊል ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ እረኛ ፡ እንደሌለሽ ፡ አትሁኚ ፣ እንደማንም ፡ መንገድ ፡ ላይ ፡ አትቅሪ ስጋሽን ፡ ጉሽም ፡ አድርገሽ ፡ ይዘሽ ፣ ወደ ፡ ርስትሽ ፡ ግቢ ፡ ጨክነሽ ችግሩን ፡ መከራውን ፡ መቅመስ ፣ ግድ ፡ ነው ፡ ብድረ ፡ በዳን ፡ ማለፍ በሜዳው ፡ በትዕግስት ፡ እሩጪ ፣ አቃተኝ ፡ ብለሽ ፡ አታቋርጬ አዝ:- ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ከመንገድ ፡ አትቅሪ ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ አትቅሪ (፪x) እርስት ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ ፣ መኖሪያ ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ ክብር ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ ፣ አክሊል ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ ዮሴፍን ፡ ወንድሞቹ ፡ የጠሉት ፣ ለአውሬ ፡ ጉድጓድ ፡ ውስጥ ፡ የጣሉት ያ ፡ ሁሉ ፡ ግፍ ፡ የደረሰበት ፣ የእግዚአብሔር ፡ ሃሳብ ፡ ስላለበት እንዲህ ፡ ያለው ፡ ምስክር ፡ እያለሽ ፣ ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ለምን ፡ ትደክሚያለሽ ፈተና ፡ ለጊዜው ፡ ያሳዝናል ፣ ኋላ ፡ ላይ ፡ መልካም ፡ ፍሬ ፡ ያፈራል አዝ:- ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ከመንገድ ፡ አትቅሪ ተይ ፡ ነፍሴ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ አትቅሪ (፪x) እርስት ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ ፣ መኖሪያ ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ ክብር ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ ፣ አክሊል ፡ አለ ፡ ተነሽ ፡ እሩጪ እግዚአብሔር ፡ የሰጠሽን ፡ ተስፋ ፣ ሚያስጥሉ ፡ ብዙ ፡ ናቸውና አንቺ ፡ ግን ፡ ታላቅ ፡ ዋጋ ፡ እንዳለሽ ፣ አትዘንጊ ፡ ምድራዊውን ፡ አይተሽ የእምነትሽን ፡ ጀማሪ ፡ ፈጻሜ ፣ ምሳሌሽን ፡ ኢየሱስን ፡ እዬ ጨርሰሽ ፡ የጀመርሺውን ፣ ተቀበይ ፡ ሽልማትሽን