Loading
Singer
በሕይወት ፡ ጐዳና ፡ ተስፋ ፡ ቆርጦ ፡ ሞትን ፡ ለሚጠብቀው እረፍትን ፡ ፍለጋ ፡ ተቅበዝብዞ ፡ ሰላሙ ፡ ለራቀው ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መፍትሄው ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሚያድነው (፪x) በራስህ ፡ ኃይልና ፡ ጉልበት ፡ ነፍስህን ፡ አታድንም በያዝከው ፡ ሃብትና ፡ ንብረት ፡ እርካታን ፡ አታገኝም ይልቅስ ፡ ቶሎ ፡ ብለህ : ና ፡ ትምክትህን ፡ ተውና ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ብለህ ፡ ተወለድ ፡ እንደገና ያኔ ፡ ነው ፡ እርካታህ ያኔ ፡ ነው ፡ ፍፁም ፡ ደስታህ (፪x) በሕይወት ፡ ጐዳና ፡ ተስፋ ፡ ቆርጦ ፡ ሞትን ፡ ለሚጠብቀው እረፍትን ፡ ፍለጋ ፡ ተቅበዝብዞ ፡ ሰላሙ ፡ ለራቀው ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መፍትሄው ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሚያድነው (፪x) በመስቀል ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ ሲሞት ፡ እዳህን ፡ ተሸክሞ ከኃጢአት ፡ ደዌ ፡ ሊያድንህ ፡ ስለአንተ ፡ እርሱ ፡ ቆስሎ ኃጢአትህን ፡ ደምስሶልሃል ፡ ንጹህ ፡ ደሙን ፡ አፍስሶ ና ፡ ልጄ ፡ ናና ፡ ይልሃል ፡ ስራህንም ፡ ጨርሶ ድምጹን ፡ ስማ ፡ ወዳጄ ፡ ተከፍቷል ፡ የምህረት ፡ ደጄ ድምጹን ፡ ስማ ፡ ወዳጄ ፡ ተከፍቷል ፡ የምህረት ፡ ደጄ በሕይወት ፡ ጐዳና ፡ ተስፋ ፡ ቆርጦ ፡ ሞትን ፡ ለሚጠብቀው እረፍትን ፡ ፍለጋ ፡ ተቅበዝብዞ ፡ ሰላሙ ፡ ለራቀው ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መፍትሄው ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሚያድነው (፪x)