Loading
Singer
የእግዚአብሔር ፡ ፈቃድ ፡ በልጁ ፡ ሊፈጸም ራሱን ፡ ዝቅ ፡ አድርጐ ፡ ወረደ ፡ ለዓለም በምድር ፡ ሊሰማ ፡ ሰላምና ፡ ደስታ ከድንግል ፡ ማሪያም ፡ ተወለደ ፡ ጌታ (፬x) አዝ፦ ተወለደ (፬x) ተወለደ (፬x) እነሆ ፡ የምስራች ፡ እነሆ ፡ የምስራች ዛሬ ፡ በዳዊት ፡ ከተማ እርሱም ፡ ክርስቶስ ፡ ጌታ ፡ የሆነ ተወለደ (፬x) ፤ ተወለደ (፬x) እረኞች ፡ ለማየት ፡ እጅጉን ፡ ጓጉለት ሰባ ፡ ሰገል ፡ መተው ፡ ወድቀው ፡ ሰገዱለት የፍጥረታት ፡ ጌታ ፡ የዓለም ፡ ሁሉ ፡ ንጉሥ ከአብ ፡ ሊያስታርቀን ፡ ተወለደ ፡ ኢየሱስ (፬x) አዝ፦ ተወለደ (፬x) ተወለደ (፬x) መላዕክት ፡ አበሰሩ ፡ የምስራቹን ፡ ቃል ዛሬ ፡ በቤቴልሄም ፡ ወንድ ፡ ልጅ ፡ ተወልዷል ምድር ፡ ዕልል ፡ ትበል ፡ ታሰማ ፡ ምሥጋና ሕዝቡን ፡ የሚታደግ ፡ መሲህ ፡ መጥቷልና (፬x) አዝ፦ ተወለደ (፬x) ተወለደ (፬x) እነሆ ፡ የምስራች ፡ እነሆ ፡ የምስራች ዛሬ ፡ በዳዊት ፡ ከተማ እርሱም ፡ ክርስቶስ ፡ ጌታ ፡ የሆነ ተወለደ (፬x) ፤ ተወለደ (፬x)