Loading
Singer
አዝ፦ አቻና ፡ ተወዳዳሪ ፡ የለህም ብቻህን ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፫x) እንዴት ፡ እንዳቆምካት ፡ ምድርና ፡ መሰረቷን በምን ፡ እንዳፀናሃት ፡ የድንጋይ ፡ ማእዘኗን ብቻህን ፡ ጌታ ፡ ነህ (፬x) የባሕር ፡ ዳር ፡ ድንበሩን ፡ ለአንተ ፡ ማን ፡ አሳየህ ሁሉ ፡ በቃልህ ፡ ሆነ ፡ ሰምቶህ ፡ እየታዘዘህ (፪x) አዝ፦ አቻና ፡ ተወዳዳሪ ፡ የለህም ብቻህን ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፫x) ከአህዛብ ፡ ጥበበኞች ፡ የሚመስልህ ፡ ማን ፡ አለ ከመንግሥታቸውም ፡ ውስጥ ፡ ተወዳዳሪ ፡ የለህ ብቻህን ፡ ጌታ ፡ ነህ (፬x) ሁሉም ፡ ፍጥረት ፡ በፊትህ ፡ ለአንተ ፡ ይንበረከካሉ ወደዱም ፡ ጠሉም ፡ ለክብርህ ፡ ወድቀው ፡ ይሰግዳሉ (፪x) አዝ፦ አቻና ፡ ተወዳዳሪ ፡ የለህም ብቻህን ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፫x) ይሄ ፡ የሰማነው ፡ ምንኛ ፡ እጅግ ፡ ጥቂት ፡ ነው የኃይሉንስ ፡ ነጐድጓድ ፡ የሚያስተውለው ፡ ማነው ብቻውን ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው (፬x) ትልቅ ፡ ነው ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሃሳቡን ፡ የሚያውቅ ፡ ማነው በሠማይም ፡ በምድር ፡ እኩያ ፡ አቻ ፡ የሌለው (፪x) አዝ፦ አቻና ፡ ተወዳዳሪ ፡ የለህም ብቻህን ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፫x) ብቻህን ፡ ጌታ ፡ ነህ (፬x)