Loading
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ተዋጊ ፡ አሄሄ እግዚአብሔር ፡ ተዋጊ ፡ ነው (፪x) ለሚታመኑበት ፡ እህህ ፡ ልጆቹን ፡ ታዳጊ በተሰለፈበት ፡ እህህ ፡ ሁሌ ፡ ድል ፡ አድራጊ እግዚአብሔር ፡ ተዋጊ ፡ አሄሄ እግዚአብሔር ፡ ተዋጊ ፡ አሄ (፪x) በገናዬን ፡ ስጡኝ ፡ አሄ ፡ እስኪ ፡ ልደርድረው ከዚህ ፡ ከወዳጄ ፡ ኤሄ ፡ ክፉን ፡ ላላቀው ሌት ፡ ተቀን ፡ ቢያደባ ፡ ጦሩን ፡ ቢሰብቅብኝ እኔ ፡ አመልጠዋለሁ ፡ አሄሄ ፡ አለ ፡ ሚዋጋልኝ አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ተዋጊ ፡ አሄሄ እግዚአብሔር ፡ ተዋጊ ፡ ነው (፪x) ለሚታመኑበት ፡ እህህ ፡ ልጆቹን ፡ ታዳጊ በተሰለፈበት ፡ እህህ ፡ ሁሌ ፡ ድል ፡ አድራጊ እግዚአብሔር ፡ ተዋጊ ፡ አሄሄ እግዚአብሔር ፡ ተዋጊ ፡ አሄ (፪x) ዳዊት ፡ አልፍ ፡ ገዳይ ፡ ሳዖል ፡ ግን ፡ ሺህ ፡ ብቻ እያሉ ፡ ቢዘፍኑ ፡ እርሱ ፡ የለው ፡ አቻ ልብህ ፡ ቅር ፡ አይበለው ፡ ክፉ ፡ አትመኝለት የሆነ ፡ እንዳሰኘው ፡ ቀን ፡ እስከወጣለት አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ተዋጊ ፡ አሄሄ እግዚአብሔር ፡ ተዋጊ ፡ ነው (፪x) ለሚታመኑበት ፡ እህህ ፡ ልጆቹን ፡ ታዳጊ በተሰለፈበት ፡ እህህ ፡ ሁሌ ፡ ድል ፡ አድራጊ እግዚአብሔር ፡ ተዋጊ ፡ አሄሄ እግዚአብሔር ፡ ተዋጊ ፡ አሄ (፪x) ሊወግሩኝ ፡ ተማማሉ ፡ ትላንት ፡ የመራኋቸው ከጨካኙ ፡ ጐልያድ ፡ ከጡቻው ፡ የዳንኳቸው ነገር ፡ ተገለባብጦ ፡ ሁሉን ፡ ተነሳ ፡ በእኔ ፡ ላይ ነገር ፡ ግን ፡ የሚመለከት ፡ ቀን ፡ ፈራጅ ፡ አለ ፡ በሰማይ በልቤ ፡ በቃ ፡ አትዘን ፡ ይልቅ ፡ በርታ ፡ በርታ ፡ በል ታያለህ ፡ ጌታ ፡ በጊዜው ፡ ሁሉንም ፡ ሲያደርገው ፡ ገለል አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ተዋጊ ፡ አሄሄ እግዚአብሔር ፡ ተዋጊ ፡ ነው (፪x) ለሚታመኑበት ፡ እህህ ፡ ልጆቹን ፡ ታዳጊ በተሰለፈበት ፡ እህህ ፡ ሁሌ ፡ ድል ፡ አድራጊ እግዚአብሔር ፡ ተዋጊ ፡ አሄሄ እግዚአብሔር ፡ ተዋጊ ፡ አሄ (፰x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.