Loading
Singer
በጉልበቴ ፡ ያለሁ ፡ ገና ፡ ያልተነካሁኝ በመንገድ ፡ አጠገብ ፡ በውጭ ፡ የታሰርኩኝ ነጻነት ፡ የሌለኝ ፡ ውርንጫ ፡ ነበርኩኝ ሳላውቅህ ፡ አውቀኸኝ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ፈታኸኝ አዝ፦ ተጠፍሬ ፡ ያየኝ ፡ ያለ ፡ ውዴታዬ ነጻነት ፡ የሰጠኝ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝታዬ ማነው ፡ ከአንተ ፡ በቀር ፡ ባለ ፡ ውለታዬ ሌላ ፡ ምን ፡ እላለሁ ፡ ተመሥገን ፡ ጌታዬ (፪x) በዚህ ፡ በጉልበቴ ፡ ለአንተ ፡ ክብር ፡ ሮጬ እባብና ፡ ጊንጡን ፡ በሥምህ ፡ ረግጬ መሸለሜን ፡ ሰምቶ ፡ ጠላት ፡ አኮረፈ አንተን ፡ በላዬ ፡ ሲያይ ፡ ጥላው ፡ ተገፈፈ አዝ፦ ተጠፍሬ ፡ ያየኝ ፡ ያለ ፡ ውዴታዬ ነጻነት ፡ የሰጠኝ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝታዬ ማነው ፡ ከአንተ ፡ በቀር ፡ ባለ ፡ ውለታዬ ሌላ ፡ ምን ፡ እላለሁ ፡ ተመሥገን ፡ ጌታዬ (፪x) ከእሥራት ፡ ፈተኸኝ ፡ በእኔ ፡ ልትቀመጥ ይህን ፡ ታላቅ ፡ ዕድል ፡ ለምስኪኑ ፡ ልትሰጥ ለመሆኑ ፡ እኔ ፡ ኧረ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነኝ ይገባኛል ፡ እንዴ ፡ ለዚህ ፡ ልትመርጠኝ አዝ፦ ተጠፍሬ ፡ ያየኝ ፡ ያለ ፡ ውዴታዬ ነጻነት ፡ የሰጠኝ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝታዬ ማነው ፡ ከአንተ ፡ በቀር ፡ ባለ ፡ ውለታዬ ሌላ ፡ ምን ፡ እላለሁ ፡ ተመሥገን ፡ ጌታዬ (፪x) ሆሴና ፡ በአርያም ፡ እያሉ ፡ ቢጮሁ ልብሳቸውንና ፡ ቅጠል ፡ ቢያነጥፉ የነገር ፡ ጀማሪ ፡ አንተ ፡ በላዬ ፡ ነህ ክብሩ ፡ የራስህ ፡ ነው ፡ ኑር ፡ ዘለዓለም ፡ ከብረህ ውርጭላው ፡ ተፈትቶ ፡ የክበር ፡ ዕቃ ፡ ሆኗል ነጻነትን ፡ ሰጥቶት ፡ ጌታው ፡ ከብሮበታል የተፈታውን ፡ ሳይሆን ፡ የፈታውን ፡ አክብሩ ሆሳዕና ፡ በሉ ፡ መንገሡንም ፡ አውሩ (፪x)