Loading
Singer
ተሸክመህ ደከመኝ የማትለኝ ከማንም ይልቅ አብልጠህ ምትጠጋኝ የማትከዳ የክፉ ቀን ወዳጄ ወደድከኝ ምንም ሳይኖር ከእጄ አንተ አንተ ግን ያው አንተ ነህ /4 በከፍታ ያው አንተ ነህ በዝቅታም ያው አንተ ነህ ከእጄ ሳጣ ያው አንተ ነህ ለዘለዓለም ወዳጄ ነህ ብዙዎች ነበሩ መመረጥ የተገባቸው አንተ ግን ምህረትህ እይታህ መች እንደ ሰው በጣም ደካማን ሰው ስትፈልግ አገኘኸኝና መንፈስህ ሸላልሞ አቆመኝ አበረታኝና የማውቀው መወደዴን ነው /2 ካንተ ውጭ ትምክህት የለኝም ከእኔ የምለው ነፋስ በሞላበት ውድማ ወድቄ አይተኸኝ ከበህ ተጠንቅቀህ አሙቀህ ብርድ እንዳያገኘኝ ንስር ጫጩቶቿን በክንፏ እንደምትደብቅ በጉያህ ሸሽገህ አኖርከኝ እንዳልሳቀቅ የማውቀው መወደዴን ነው /2 ካንተ ውጭ ትምክህት የለኝም ከእኔ የምለው አመሰግንሃለሁ /3 ክብርን በአንተ አይቻለሁ