Loading
Singer
አዝ፦ ኑሮዬ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ሸለቆ ፡ ቢሆን ፡ ተራራ የደስታ ፡ ቢሆን ፡ የዕንባ ትሻለኛለህ ፡ አባባ ሊያጠግብ ፡ ኩርማን ፡ እንጀራ ቀንና ፡ ሌሊት ፡ ብሰራ አለቀ ፡ ኃይሌ ፡ ጉልበቴ በክንድህ ፡ ጥቂት ፡ ዘመኔ በአንተ ፡ ቤት ፡ ልረፍ ፡ መድህኔ (፪x) አዝ፦ ኑሮዬ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ሸለቆ ፡ ቢሆን ፡ ተራራ የደስታ ፡ ቢሆን ፡ የዕንባ ትሻለኛለህ ፡ አባባ ከዛሬ ፡ ነገ ፡ ይሻል ፡ ብዬ ብዙ ፡ ሮጥኩኝ ፡ ጨርቄን ፡ ጥዬ በዓለም ፡ ያየሁት ፡ አበሳ እስከመቼም ፡ አይረሳ ከእንግዲህ ፡ በቃ ፡ ሩጫዬ መስቀልህ ፡ ሆኗል ፡ ምርጫዬ (፪x) አዝ፦ ኑሮዬ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ሸለቆ ፡ ቢሆን ፡ ተራራ የደስታ ፡ ቢሆን ፡ የዕንባ ትሻለኛለህ ፡ አባባ ክፉ ፡ ዓለም ፡ ክብር ፡ የጐደላት ጦር ፡ እንጂ ፡ ሰላም ፡ የሌላት ሰው ፡ በአምላክ ፡ አምሳል ፡ ተፈጥሮ ወደ ፡ አውሬነት ፡ ተቀይሮ እርስ ፡ በርስ ፡ ስታብላላ በውሸት ፡ ዕውቀት ፡ አታላ (፪x) አዝ፦ ኑሮዬ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ሸለቆ ፡ ቢሆን ፡ ተራራ የደስታ ፡ ቢሆን ፡ የዕንባ ትሻለኛለህ ፡ አባባ የዚህ ፡ ዓለም ፡ ጌታ ፡ ከመሆን ሰማይን ፡ ምድርን ፡ ከመግዛት እራስን ፡ ላንተ ፡ አስገዝቶ ድሃ ፡ ተብሎ ፡ መጠራት ክብር ፡ እንደሆነ ፡ አወቅሁ ፡ ጠንቅቄ (፪x) በቤትህ ፡ ልኑር ፡ ማቅቄ አዝ፦ ኑሮዬ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ሸለቆ ፡ ቢሆን ፡ ተራራ የደስታ ፡ ቢሆን ፡ የዕንባ ትሻለኛለህ ፡ አባባ