Loading
Singer
የምትሄድበት ፡ መንገድ ፡ ጨለማ ፡ ቢሆንብህም በኃይለኛ ፡ ውሃ ፡ ውስጥ ፡ ሳትፈልግ ፡ ብታልፍም ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ያለው ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው መንገድ ፡ አዘጋጅቶ ፡ መውጫ ፡ ሚያበጅ ፡ ነው (ሃሌሉያ) አዝ፦ ተስፋ ፡ ቆርጦ (ተስፋ ፡ ቆርጦ) ለሚያዘግም (ለሚያዘግም) ፡ ለሚሄደው ፡ በጨለማ አምላክ ፡ አለ (አምላክ ፡ አለ) መሪ ፡ አለ (መሪ ፡ አለ)፡ ጩኸትህን ፡ ሁሉ ፡ የሚሰማ ተስፋ ፡ አትቁረጥ (ተስፋ ፡ አትቁረጥ) ወንድሜ ፡ ሆይ (ወንድሜ ፡ ሆይ) ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ይወድሃል ወደ ፡ እቅፉ ፡ (ወደ ፡ እቅፉ) ጉያ ፡ ግባ ፡ (ጉያ ፡ ግባ) ፡ ኧረፍቱ ፡ ይመራሃል ተራራው ፡ ከፊት ፡ ሆኖ ፡ የሩቁን ፡ ቢጋርድብሽ ተስፋሽ ፡ ሁሉ ፡ ጨልሞ ፡ የተተውሽ ፡ ሲመስልሽ ታምነሽ ፡ ጸንተሽ ፡ ቁሚ (ጸንተሽ ፡ ቁሚ) በሰራዊት ፡ ጌታ ፡ ሁሉን ፡ በሚያሸንፍ (በሚያሸንፍ) ሁሉን ፡ በሚረታ (ሃሌሉያ) አዝ፦ ተስፋ ፡ ቆርጦ (ተስፋ ፡ ቆርጦ) ለሚያዘግም (ለሚያዘግም) ፡ ለሚሄደው ፡ በጨለማ አምላክ ፡ አለ (አምላክ ፡ አለ) መሪ ፡ አለ (መሪ ፡ አለ) ፡ ጩኸትሽህን ፡ ሁሉ ፡ የሚሰማ ተስፋ ፡ አትቁረጥ(ተስፋ ፡ አትቁረጥ) ወንድሜ ፡ ሆይ (እህቴ ፡ ሆይ) ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ይወድሻል ወደ ፡ እቅፉ ፡ (ወደ ፡ እቅፉ) ጉያ ፡ ግባ ፡ (ጉያ ፡ ግባ) ፡ ኧረፍቱ ፡ ይመራሻል እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ በፍቅሩ ፡ እውነተኛ ለመንጋው ፡ የሚራራ ፡ ታማኝ ፡ የሆነ ፡ ኧረኛ ከልብ ፡ ለሚጠሩት ፡ ፈጥኖ ፡ የሚደርስ ለጥያቄ ፡ ሁሉ ፡ መልስ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ (ሃሌሉያ)