Loading
Singer
አዝ፦ እኔስ ፡ ተስፋ ፡ አለኝ (፬x) የተገባልኝ ፡ የተስፋ ፡ ቃል ፡ አለኝ ተስፋዬም አንድነው ፡ ተስፋን ፡ የሰጠኝ (፪x) የገባልኝን ፡ ቃሉ ፡ ይፈጽማልና ይዋሽ ፡ ዘንድ ፡ ጌታ ፡ ሰው ፡ አይደለምና እውነት ፡ ተናጋሪ ፡ ያለውን ፡ የሚፈጽም ቃልኪዳን ፡ አክባሪ ፡ እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ የለም ቃልኪዳን ፡ አክባሪ ፡ እንደ ፡ እርሱ ፡ ያለ ፡ የለም (፬x) አዝ፦ እኔስ ፡ ተስፋ ፡ አለኝ (፬x) የተገባልኝ ፡ የተስፋ ፡ ቃል ፡ አለኝ ተስፋዬም: አንድነው ፡ ተስፋን ፡ የሰጠኝ (፪x) እኔ ፡ የምመካበት ፡ የምታመንበት ተስፋዬ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ የምደገፍበት አለኝ ፡ አለኝ ፡ የምለው ፡ ተስፋን ፡ የሰጠኝ ተስፋዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ሌላው ፡ አይሆነኝም ተስፋዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ሌላው ፡ አይሆነኝም (፬x) አዝ፦ እኔስ ፡ ተስፋ ፡ አለኝ (፬x) የተገባልኝ ፡ የተስፋ ፡ ቃል ፡ አለኝ ተስፋዬም አንድነው ፡ ተስፋን ፡ የሰጠኝ (፪x) ተስፋ ፡ እንደሌለው ፡ ሰው ፡ ተስፋዬን ፡ አልቆርጥም ብዙ ፡ ተስፋ ፡ አለው ፡ መድሃኒያዓለም ያየልኝ ፡ ብዙ ፡ አለ ፡ ለእኔ ፡ የተመኘው ታዲያለሁ ፡ በቃ ፡ ተስፋዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ታዲያለሁ ፡ በቃ ፡ ተስፋዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፬x) አዝ፦ እኔስ ፡ ተስፋ ፡ አለኝ (፬x) የተገባልኝ ፡ የተስፋ ፡ ቃል ፡ አለኝ ተስፋዬም: አንድነው ፡ ተስፋን ፡ የሰጠኝ (፪x)