Loading
Singer
ተሰሚ ፡ ነህ ፡ በሰማይ ፡ በምድር ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ሚንበረከክልህ የፈጠርከን ፡ እንሰግድልሃለን ሞገስህን ፡ ክብርህን ፡ እያየን ይሹሩን ፡ ሆይ ፡ በሰማያት ፡ ላይ ፡ ለእረድኤትህ በደመናት ፡ ላይ ፡ እንደሚሄድ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም ኧረ እንደርሱ ፡ ያለ ፡ ቢፈለግም ፡ የለም (፪x) ዘመንህ ፡ ዘላለም ፡ ከቶ ፡ አታረጅም አምሳያ ፡ የለህም ፡ መቼም ፡ አትተካም አዬዬ ፡ መቼም ፡ አትተካም ፊትህ ፡ እንደ ፡ ፀሐይ ፡ በሀይል ፡ የሚያበራ ከዋክብት ፡ ጨረቃን ፡ ደመናን ፡ የሰራህ አዬዬ ፡ ፀሐይን፡ የሰራህ የአማልክቱ ፡ አምላካቸው ፡ ነህ የፍጥረት ፡ ገዢ ፡ የዓለማት ፡ ንጉሥ ፡ ነህ ወሰን ፡ የሌለህ ፡ ስራህ ፡ እረቂቅ የማትታወቅ ፡ የሆንህ ፡ እጅግ ፡ ታላቅ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ቢፈለግም ፡ የለም ኧረ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ታላቅ ፡ አምላክ ፡ የለም እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ቢፈለግም ፡ የለም ኧረ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ አይኖርም ፡ ዘላለም ተሰሚ ፡ ነህ ፡ በሰማይ ፡ በምድር ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ሚንበረከክልህ የፈጠርከን ፡ እንሰግድልሃለን ሞገስህን ፡ ክብርህን ፡ እያየን ይሹሩን ፡ ሆይ ፡ በሰማያት ፡ ላይ ፡ ለእረድኤትህ በደመናት ፡ ላይ ፡ እንደሚሄድ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም እንደርሱ ፡ ያለ ፡ ቢፈለግም ፡ የለም (፪x) የዓለም ፡ ሁሉ ፡ መሪ ፡ ብርቱ ፡ ነህ ፡ ሀይለኛ ከሁሉ ፡ ቀዳሚ ፡ የሌለህ ፡ ፊተኛ አዬዬ ፡ የሌለህ ፡ ፊተኛ ይሁን ፡ ባልከው ፡ ቃልህ ፡ ሁሉ ፡ ተፈጠረ እቅድህ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ስራህም ፡ ያማረ አዬዬ ፡ ስራህም ፡ ያማረ የአማልክቱ ፡ አምላካቸው ፡ ነህ የፍጥረት ፡ ገዢ ፡ የዓለማት ፡ ንጉሥ ፡ ነህ ወሰን ፡ የሌለህ ፡ ስራህ ፡ እረቂቅ የማትታወቅ ፡ የሆንህ ፡ እጅግ ፡ ታላቅ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ቢፈለግም ፡ የለም ኧረ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ታላቅ ፡ አምላክ ፡ የለም እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ቢፈለግም ፡ የለም ኧረ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ አይኖርም ፡ ዘላለም (፪x)