Loading
Singer
አነጋልኝ ፡ ዛሬን ፡ በዕድሜዬ ፡ ጨመረው (፪x) በስሙ ፡ ዋጅቼ ፡ ቀኑን ፡ ልጀምረው (፪x) አይ ፡ አይ ፡ አይ ፡ አይ ሳላመልክ ፡ በከንቱ ፡ አይ አይለፍ ፡ ዕለቱ ፡ አይ ፡ አይ ፡ አይ አምልኪው ፡ ተብዬ ፡ ተነግሮኝ ፡ ጀምሬ አምልኩት ፡ እላለሁ ፡ እኔ ፡ ደግሞ ፡ ዛሬ አምልኪው ፡ አምልኪው ፡ ተብዬ ፡ ጀምሬ አምልኩት ፡ እላለሁ ፡ እኔ ፡ ደግሞ ፡ ዛሬ እናም ፡ እግዚአብሔር ፡ የሚመለከው ጠጋ ፡ ተብሎ ፡ ነው እንዴ ፡ እግዚአብሐር ፡ የሚመለከው በእውነት ፡ በመንፈስ ፡ ነው አዝ፦ ማደሪያው ፡ ስር ፡ እሆናለሁ ፡ እንጂ ዙፋኑ ፡ ስር ፡ እሰግዳለሁ ፡ እንጂ ተሳልሜ ፡ አልሄድም ፡ ከደጅ (፬x) ሃያራቱ ፡ ሽማግሌዎች ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ እልፍ ፡ አእላፍ ፡ መላእክቱ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ምስጋና ፡ አለው ፡ የተረፈ ፡ ከኔ ፡ የሚሻው ፡ ከቃሌ ፡ ባለፈ አምልኮ ፡ አለው ፡ የተረፈ ፡ እኔም ፡ ልዘምር ፡ ከቃሌ ፡ ባለፈ ሰው ፡ በከንፈሩ ፡ አምልኮ ልቡን ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ቢያርቀው ልብን ፡ የሚመረምረው የአፉን ፡ ቃል ፡ ብቻ ፡ አይሰማው (፪x) አዝ፦ ማደሪያው ፡ ስር ፡ እሆናለሁ ፡ እንጂ ዙፋኑ ፡ ስር ፡ እሰግዳለሁ ፡ እንጂ ተሳልሜ ፡ አልሄድም ፡ ከደጅ (፬x) ለልቤ ፡ ጌታ ፡ ከልቤ ለልቤ ፡ ንጉስ ፡ ከልቤ እስኪ ፡ ልዘምር ፡ ከልቤ ዛሬም ፡ እንደልጅነቴ (፪x) እኔ ፡ ያመንኩትን ፡ አውቃለሁኝ ፡ ልንገረው ፡ የሚሻ እኔ ፡ ያመንኩትን ፡ አውቃለሁኝ ፡ ልንገረው ፡ የሚሻ ጌታ ፡ ነው ፡ የመጀመሪያ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የመጨረሻ አምላክ ፡ ነው ፡ የመጀመሪያ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ የመጨረሻ (፪x) ሃይለኛ ፡ የመጀመሪያ ፡ ሃይለኛ ፡ የመጨረሻ ታዋቂ ፡ የመጀመሪያ ፡ ታዋቂ ፡ የመጨረሻ ዝነኛ ፡ የመጀመሪያ ፡ ዝነኛ ፡ ነው ፡ የመጨረሻ ንጉስ ፡ ነው ፡ የመጀመሪያ ፡ ንጉስ ፡ ነው ፡ የመጨረሻ ጌታ ፡ ነው ፡ የመጀመሪያ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የመጨረሻ አምላክ ፡ ነው ፡ የመጀመሪያ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ የመጨረሻ