Loading
Singer
ሥምህ ፡ በአፌ ፡ ላይ ፡ ይጣፍጠኛል ሁሌ ፡ ስጠራው ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ ይለኛል የትኛው ፡ ሥም ፡ ነው ፡ የተወደደው ጠዋት ፡ ተወርቶ ፡ ማታ ፡ የሚወርደው እንዳየነው የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ግን ፡ ሥሙ ፡ ይለያል ሁሌ ፡ ስጠራው ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ጠረነ ፡ ልዩ ፡ ማዕዛ ፡ ያለው የአባትዬ ፡ ሥም ፡ ልክ ፡ እንደ ፡ ማር ፡ ነው እንደ ፡ ማር እንደ ፡ ማር ፡ ኧረ ፡ እንደ ፡ ማር (፬x) እኔስ ፡ ቆርጫለሁ ፡ ለጌታ ፡ ዘንድሮ ሕይወት ፡ ተገለጠ ፡ በራልኝ ፡ በቶሎ ዋጋዬን ፡ ተምኜ ፡ ስለወጣሁኝ እመቅደሱ ፡ ደጃፍ ፡ ወስዳችሁ ፡ ጣሉኝ ትርፌማ ፡ ቅባት ፡ ነው ፡ ቅባት ፡ በመንገዴ ያገኘኛል ፡ አልኩኝ ፡ ያየኛል ፡ አባቴ ዋጋዬን ፡ ተምኜው ፡ ስለወጣሁኝ እመቅደሱ ፡ ደጃፍ ፡ ወስዳችሁ ፡ ጣሉኝ (፫x) አሄ ፡ ኦሆ አርዶ ፡ የወጣ ፡ ሰው ፡ ከቶ ፡ አይመለስም ጌልጌላ ፡ ተነስቶ ፡ ቤቴል ፡ ላይ ፡ አይቆምም እያሪኮን ፡ አልፎ ፡ ዮርዳኖስ ፡ ይዘልቃል እጥፍ ፡ መንፈስ ፡ ይዞ ፡ በክብር ፡ ይመለሳል በኤልያስ ፡ እጅ ፡ ላይ ፡ ውኃ ፡ የሚያፈሰው አስራ ፡ ሁለት ፡ ጥማድ ፡ በሬ ፡ አረደው በሕያው ፡ ልብሱ ፡ ምን ፡ አለ ፡ የተከተለው ሞኝ ፡ ሆኖ ፡ አይደለም ፡ ክብር ፡ አይቶ ፡ ነው ቅባት ፡ አይቶ ፡ ነው ፡ ክብር ፡ አይቶ ፡ ነው ጌልጌላ ፡ ሸለፈትክ ፡ የተገረዘው ቤቴል ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቤት ፡ የተጸለየው እያሪኮም ፡ ይናድ ፡ በጩኸት ፡ ይፍረስ ዮርዳኖስ ፡ ልጠመቅ ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ አባናና ፡ ፋርፋን ፡ አልል ፡ እንደ ፡ ሰው ዮርዳኖስ ፡ ይበልጣል ፡ የደፈረሰው ብቅ ፡ ትልቅ ፡ ብዬል ፡ ከለምጽ ፡ እነጻለሁ አንተ ፡ ያልከኝ ፡ ቦታ ፡ ፈውስ ፡ አገኛለሁ (፪x) መዳን ፡ አገኛለሁ ዘመኔ ፡ እንደ ፡ ሻማ ፡ እንደ ፡ ጧፍ ፡ ቢነድ ያንስበታል ፡ እንጂ ፡ መች ፡ ይበዛበት እርሱማ ፡ ተዋርዶ ፡ በሞቱ ፡ አክብሮኝ ለኢየሱሴ ፡ ኖሬ ፡ እስቲ ፡ ይለይልኝ አሸፈተው ፡ ልቤን ፡ ኢየሱስን ፡ ወዶ የሠማይ ፡ አስባለኝ ፡ የምድሩን ፡ አስንቆ ልቤ ፡ ትዝታዬም ፡ እርሱ ፡ ጋር ፡ ቀረና ሁሉንም ፡ አሳቀኝ ፡ የእርሱ ፡ በለጠና ክብር ፡ በለጠና ፡ ቅባት ፡ በለጠና ሞኝ ፡ ነህ ፡ ይሉኛል ፡ የታል ፡ ሞኝነቴ አተረፈኩኝ ፡ እንጂ ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ጉዳቴ ኢየሱስን ፡ ይዤ ፡ እኔስ ፡ አትርፊያለሁ ምድር ፡ ተቀምጬ ፡ ቤቴ ፡ በሠማይ ፡ ነው ይኸውልህ ፡ ልቤን ፡ እንካ ፡ ውሰደው አንተ ፡ ጋር ፡ ይቀመጥ ፡ የእኔ ፡ ከንቱ ፡ ነው ሁሉንም ፡ ሰብስቤ ፡ ለአንተ ፡ ሰጠሁና አንተን ፡ አንተን ፡ አልኩኝ ፡ የአንተ ፡ በለጠና መንፈስ ፡ በለጠና ፡ ቅባት ፡ በለጠና