Loading
Singer
ተራራው ግዙፍ ቢመስል ለእኔ እንጂ ለአንተ አይደለም በፊትህ ከባድ የሚሆን የማትችለው አንድ እንኳን የለም እግዚአብሔር አንተ ኃያል ነህ ሁሉ ለአንተ ቀላል ነው ስታዝዘው የማይታዘዝህ ኤረ ከቶ የቱ ነው አምላኬ አንተ ኃያል ነህ ሁሉ ለአንተ ቀላል ነው ስታዝዘው የማይታዘዝህ ኤረ ከቶ ምንድር ነው ፩) አንድ ነገር ሰማሁ እኔም አመንሁ እርሱን ኃይል የአንተ ብቻ የአንተ እንደሆነ ኃይል የአንተ ብቻ የአንተ እንደሆነ የሚጥል የሚያነሳ የሚገድል የሚያድን ኃይል የአንተ ብቻ የአንተ እንደሆነ ኃይል የአንተ ብቻ የአንተ እንደሆነ አንተ ብርቱ ጌታ ከሆንህ የእኔ አባት ልረፍብህ እንጂ ልጠጋ በእምነት አንተ ብርቱ ጌታ ከሆንህ የእኔ አምላክ ሁሉን ለአንተ ትቼ ዝም ብዬ ላምልክህ ተራራው ግዙፍ... ፪) የሰው ልጅ ያየለ ቢመስለው በዕውቀቱ ከፀሐይዋ በታች ነገር ሁሉ ከንቱ ከፀሐይዋ በታች ነገር ሁሉ ከንቱ አንተ ግን ጌታ ሆይ ለዘላለም ያው ነህ ሥራህ ሁሉ ግሩም ድንቅ የሆነልህ ሥራህ ሁሉ ግሩም ድንቅ የሆነልህ አንተ ብርቱ ጌታ ... ተራራው ገዝፎ ቢታይ ለእኔ እንጂ ለአንተ አይደለም በፊትህ ከባድ የሚሆን የማትችለው አንድ እንኳን የለም እግዚአብሔር አንተ ኃያል ነህ ሁሉ ለአንተ ቀላል ነው ስታዝዘው የማይታዘዝህ ኤረ ከቶ የቱ ነው አምላኬ አንተ ኃያል ነህ ሁሉ ለአንተ ቀላል ነው ስታዝዘው የማይታዘዝህ ኤረ ከቶ ምንድር ነው