Loading
Singer
አዝ፦ ተቀይሯል ፡ ሙሉ ፡ አድራሻዬ ከጌታ ፡ ጋር ፡ ሆኗል ፡ ውሎዬ አትፈላልጉኝ ፡ የለሁም ፡ እዚያ ስላገኘሁ ፡ የነፍሴን ፡ ማረፊያ (፪x) ትርፉ ፡ ድካም ፡ ሁልጊዜ ፡ እሮሮ ስቆ ፡ ማልቀስ ፡ የዚህ ፡ ዓለም ፡ ኑሮ እዚም ፡ እዚያም ፡ ደስታ ፡ ለማግኘት ገላገለኝ ፡ ከመንከራተት አዝ፦ ተቀይሯል ፡ ሙሉ ፡ አድራሻዬ ከጌታ ፡ ጋር ፡ ሆኗል ፡ ውሎዬ አትፈላልጉኝ ፡ የለሁም ፡ እዚያ ስላገኘሁ ፡ የነፍሴን ፡ ማረፊያ (፪x) አዋጥቶኛል ፡ እርሱን ፡ ማለቴ እረፍት ፡ ሆነኝ ፡ ሰላም ፡ ለቤቴ እጅ ፡ እግሬን ፡ የቆለፈ ፡ ኃጢያቴ በጣጥሶታል ፡ እስራቴን አዝ፦ ተቀይሯል ፡ ሙሉ ፡ አድራሻዬ ከጌታ ፡ ጋር ፡ ሆኗል ፡ ውሎዬ አትፈላልጉኝ ፡ የለሁም ፡ እዚያ ስላገኘሁ ፡ የነፍሴን ፡ ማረፊያ (፪x) ሄድኩኝ ፡ በቃ ፡ ተከትየው መድኃኒቴን ፡ ወድጄው ሳልመለስ ፡ ፊቴን ፡ ላላዞር ወስኛለሁ ፡ በእግሩ ፡ ሥር ፡ መኖር አዝ፦ ተቀይሯል ፡ ሙሉ ፡ አድራሻዬ ከጌታ ፡ ጋር ፡ ሆኗል ፡ ውሎዬ አትፈላልጉኝ ፡ የለሁም ፡ እዚያ ስላገኘሁ ፡ የነፍሴን ፡ ማረፊያ (፪x) የቀድሞ ፡ ታሪኬን ፡ ትታችሁ አውሩት ፡ የዛሬውን ፡ ባካችሁ እንዴት ፡ እንዳዳነኝ ፡ መስክሩ ይሄ ፡ ነው ፡ ድንቅና ፡ ተዓምሩ አዝ፦ ተቀይሯል ፡ ሙሉ ፡ አድራሻዬ ከጌታ ፡ ጋር ፡ ሆኗል ፡ ውሎዬ አትፈላልጉኝ ፡ የለሁም ፡ እዚያ ስላገኘሁ ፡ የነፍሴን ፡ ማረፊያ (፪x) መላ ፡ ያጣ ፡ የተጨነቀ ተስፋው ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ያለቀ ይምጣ ፡ ምላሽ ፡ አለ ፡ ኢየሱስ ፡ ጋር አለቀልኝ ፡ ያለ ፡ የሰጋ አዝ፦ ተቀይሯል ፡ ሙሉ ፡ አድራሻዬ ከጌታ ፡ ጋር ፡ ሆኗል ፡ ውሎዬ አትፈላልጉኝ ፡ የለሁም ፡ እዚያ ስላገኘሁ ፡ የነፍሴን ፡ ማረፊያ (፪x)