Loading
Singer
Updated 8/4/2026
የኃያላን ፡ ኃያል ፡ ንጉሥ ፡ የሆንከው ብርሃንን ፡ እንደልብስ ፡ የተላበስከው ሁሉም ፡ በዙፋንህ ፡ ስር ፡ ይወድቁልሃል ኃይለኛው ፡ እግዚአብሔር ፡ ብለው ፡ ይጠሩሃል አዝ፦ ጥንትም ፡ ያለህ ፡ ዛሬም ፡ ያለህ ወደፊትም ፡ ትኖራለህ ፡ ባኃይል ፡ በግርማ ፡ ታበራለህ ትከብራለህ ፡ ትገናለህ ፡ ትደምቃለህ ፡ ከፍ ፡ ትላለህ ኃይልህን ፡ ለብሰህ ፡ በዙፋንህ ፡ ትጸናለህ ሊውጠን ፡ ተነስቶ ፡ እንደሚያገሳ ፡ አንበሳ የጠላት ፡ ሠራዊት ፡ እልፍ ፡ ሆኖ ፡ ተነሳ ሰልፉን ፡ ድል ፡ አድራጊ ፡ የአርያም ፡ እሳት ፈጥኖ ፡ ደረሰልን ፡ ኢየሱስ ፡ የእኛ ፡ አባት አዝ፦ ጥንትም ፡ ያለህ ፡ ዛሬም ፡ ያለህ ወደፊትም ፡ ትኖራለህ ፡ ባኃይል ፡ በግርማ ፡ ታበራለህ ትከብራለህ ፡ ትገናለህ ፡ ትደምቃለህ ፡ ከፍ ፡ ትላለህ ኃይልህን ፡ ለብሰህ ፡ በዙፋንህ ፡ ትጸናለህ ዘመናት ፡ ሲያልፉ ፡ ታሪክ ፡ ሲለዋወጥ በዙፋኑ ፡ አርፎ ፡ ጸንቶ ፡ የሚቀመጥ የተዘጋውን ፡ ማኅተም ፡ ብቻውን ፡ የፈታ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ አዝ፦ ጥንትም ፡ ያለህ ፡ ዛሬም ፡ ያለህ ወደፊትም ፡ ትኖራለህ ፡ ባኃይል ፡ በግርማ ፡ ታበራለህ ትከብራለህ ፡ ትገናለህ ፡ ትደምቃለህ ፡ ከፍ ፡ ትላለህ ኃይልህን ፡ ለብሰህ ፡ በዙፋንህ ፡ ትጸናለህ ጠቢቡን ፡ ኃያሉን ፡ ማንንም ፡ ሳይፈራ የጽድቅ ፡ ስራውን ፡ በዓለም ፡ የሚሰራ ሃኪም ፡ ያልቻለውን ፡ በሽታ ፡ ሚፈውስ ኢየሱስ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ የዓለም ፡ ሁሉ ፡ ንጉሥ አዝ፦ ጥንትም ፡ ያለህ ፡ ዛሬም ፡ ያለህ ወደፊትም ፡ ትኖራለህ ፡ ባኃይል ፡ በግርማ ፡ ታበራለህ ትከብራለህ ፡ ትገናለህ ፡ ትደምቃለህ ፡ ከፍ ፡ ትላለህ ኃይልህን ፡ ለብሰህ ፡ በዙፋንህ ፡ ትጸናለህ ኢየሱስ ፡ በዓለም ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ ታወቀ ዝናውም ፡ ገነነ ፡ ሄደ ፡ እየደመቀ እናንተ ፡ አጋንንቶች ፡ ምን ፡ ሊውጣቹህ ፡ ነው ሂዱ ፡ ተቃጠሉ ፡ ስፍራቹህ ፡ ጥልቁ ፡ ነው አዝ፦ ጥንትም ፡ ያለህ ፡ ዛሬም ፡ ያለህ ወደፊትም ፡ ትኖራለህ ፡ ባኃይል ፡ በግርማ ፡ ታበራለህ ትከብራለህ ፡ ትገናለህ ፡ ትደምቃለህ ፡ ከፍ ፡ ትላለህ ኃይልህን ፡ ለብሰህ ፡ በዙፋንህ ፡ ትጸናለህ ኃይልህን ፡ ለብሰህ ፡ በማደሪያህ ፡ ትኖራለህ ኃይልህን ፡ ለብሰህ ፡ በመንግሥትህ ፡ ትኖራለህ